Connect with us

መጪው ምርጫ ነሐሴ 10 ቀን እንደሚካሄድ በጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ተመለከተ

መጪው ምርጫ ነሐሴ 10 ቀን እንደሚካሄድ በጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ተመለከተ

ፓለቲካ

መጪው ምርጫ ነሐሴ 10 ቀን እንደሚካሄድ በጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ተመለከተ

መጪው ምርጫ ነሐሴ 10 ቀን እንደሚካሄድ በጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ተመለከተ

– የምረጡኝ ዘመቻ ሚያዚያ 27 ይጀምራል፣

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የዘንድሮ ምርጫ የሚከናወንበት የሚያሳይ ጊዜያዊ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በዛሬው ዕለት ውይይት እያደረገ መሆኑ ተሰማ፡፡ በጊዜያዊ ሰሌዳው መሠረት የዘንድሮ ምርጫ ድምጽ መስጫ ዕለት ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚሆን ተመልክቷል፡፡ በተጨማሪም የመራጮች ምዝገባ ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዚ 28 ቀን 2012 ዓ.ም. የእጩዎች ምዝገባ ጊዜ ከሚያዚያ 13 ቀን እስከ ሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም፣ የምረጡኝ ዘመቻ ጊዜ ከሚያዚያ 27 እስከ ነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም፣ የምርጫ ድምጽ መስጫ ዕለት ነሐሴ 10 ቀን ሲሆን ቦርዱ የተረጋገጠ ውጤት ማሳወቂያ ቀን ከነሐሴ 11 እስከ 20/2012 ዓ.ም እንደሚሆን ተጠቅሷል፡፡ በጊዜ ሰሌዳው እና አፈፃፀሙ ላይ እየተካሄደ ባለው ውይይት ከተነሱ ተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች እና አስተያየቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

የመራጮች ምዝገባ ጊዜ 30 ቀናት እንደሚያንስ፣ የእጩ ምዝገባ ቀናት አንሷል፣ ቢታሰብበት፣ ቀኑ ክረምት ላይ በመዋሉ ለማስፈፀም ያስቸግራል፣ ጥቅምት/ህዳር ላይ ለምን አይሆንም? በምርጫ ዘመቻ ወቅት ወከባ እንዳይፈጠር ቦርዱ ዝግጅት ቢያደርግ? የምረጡኝ ቅስቀሳ ቀናት ያንሳሉ፣ ከአሁን ጀምሮ ቅስቀሳ የጀመሩ ፓርቲዎችም አሉ፣ ቦርዱ ምን ይላል? ፓርቲዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ የሚደረደሩበት ቅደም ተከተል በእጣ ይሆናል ማለት ምን ማለት ነው?

በምርጫ ቦርድ አመራር አካላት ለቀረቡት ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የመራጮች ምዝገባ በሕግ የተቀመጠ 30 ቀን መሆኑን የእጩ ምዝገባ ቀናት በህግ የተቀመጠ መልኩ እንደሚታይ፣ አስፈላጊ ከሆነ ቀናት መጨመሩን ቦርዱ ሊያየው ይችላል ግን በእቅዱ ላይ የተቀመጠው ቀን ለፓርቲዎች እንደማያንስ እንደውም ጫና የሚሆነው ቦርዱ ላይ መሆኑን ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ነሐሴ ላይ ምርጫው መካሄዱ ቦርዱ ወዶ የገባበት አይደለም፣ ግንቦት ለማድረግ ስላልተቻለ ነው፣ ብዙ የተዘረዘሩ ለውጦች እያደረገ እንደሆነ ቦርዱ ገልፆአል፡፡ ስለዚህ ግንቦት ላይ ማድረግ የሚቻል አይደለም። አፈፃፀሙ ክረምት በመሆኑ ብዙ ችግር እንደሚገጥመው እሙን ነው ከክልል መንግስታት፣ ከፌደራል መንግስትና ሌሎች ተቋማት ቦርዱ የሎጀስቲክስ ድጋፍ ጠይቆ ለማስፈፀም ጥረት ያደርጋል። ከመስከረም ካለፈ ደሞ የህግ ጥሰት ይፈጥራል፡፡ ስለዚህ ወደፊት መግፋት አለመቻሉ ተነግሮአል፡፡

የዘመቻ ጊዜ ከወከባ እና ችግር እንዳይኖር ቦርዱ ጥረት ያደርጋል፣ ከዚህ በፊት ፓርቲዎች ችግር ሲገጥማቸው ቦርዱ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፣ አሁን ይህንን ድጋፍ ለማስፋት በምርጫ ዘመቻ ወቅት የራሱ ዴስክ አዘጋጅቶ ተቋማዊ ድጋፍ እንደሚያደርግ የቦርድ አባላቱ ጠቅሰዋል፡፡

የምረጡኝ ቅስቅሳ አሁን መጀመር አይቻልም፣ የተሰጠው ሶስት ወር በላይ ግን በቂ ነው፣ ከአሁኑ ቅስቀሳ የጀመሩ አሉ ለተባለው ውይይት እና ንግግር ከህዝብ ጋር ማድረግ ይቻላል ፣ እኔን ምረጡኝ የሚል ዘመቻ ግን መጀመር አይቻልም፣ ያንን የሚያደርጉ ፓርቲዎች ላይ ቦርዱ ማጣራት ያደርጋል።

ፓርቲዎች የድምፅ መስጫ ወረቀት ቅደም ተከተል ሲባል የሚደረደሩበት መንገድ በእጣ የሚወሰን ይሆናል እንጂ ከዚህ በፊት እንደነበረው አይሆንም። እጣው ላይ በሚደርሳቸው ቅደም ተከተል መሰረት ፓርቲዎች የድምፅ መስጫ ወረቀቱ ላይ በቅደም ተከተል እንደሚቀመጡ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top