Connect with us

ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ከ100 የፎርብስ መጽሔት የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች አንዷ ሆነው ተመረጡ

ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ከ100 የፎርብስ መጽሔት የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች አንዷ ሆነው ተመረጡ
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ከ100 የፎርብስ መጽሔት የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች አንዷ ሆነው ተመረጡ

ከዝነኛውና አንጋፋው ‹‹ፎርብስ (Forbes)›› መጽሔት የ2019 ዓ.ም 100 የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል ብቸኛዋ አፍሪካዊት – የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

በዝርዝሩ ውስጥ ከሰሜን አሜሪካ 50፣ ከአውሮፓ 23፣ ከእስያና ፓሲፊክ 21፣ ከመካከለኛው ምስራቅ 3፣ ከደቡብ አሜሪካ 2 ሴቶች ሲካተቱ አንጋፋዋ ዲፕሎማት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከአፍሪካ በብቸኝነት ተመርጠዋል፡፡ ፕሬዝደንት ሳህለወርቅ ከባለፈው ዓመት (2018) የመጽሔቱ 100 የዓለማችን ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች መካከልም አንዷ ነበሩ፡፡

በመጽሔቱ (የ2019 ዓ.ም) ምርጫ መሰረት ከሴቶች የጀርመኗ መራኂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል፣ ፈረንሳዊቷ የአውሮፓ ማዕከላዊ ባንክ ፕሬዝደንት ክርስቲን ላጋርድ እና ዴሞክራቷ የአሜሪካ የተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ እንደቅደምተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡

በአጠቃላይ (በወንድም በሴትም) ደግሞ የቻይና፣ የሩስያና የአሜሪካ ፕሬዝደንቶች ቀዳሚዎቹን 3 ደረጃዎች ተቆጣጥረዋቸዋል፡፡

አንጌላ ሜርክል፣ ጄፍ ቤዞስ፣ የሮም ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ፣ ቢል ጌትስ፣ አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ሰልማን፣ ናሬንድራ ሞዲ እና ላሪ ፔጅ ከ4ኛ እስከ 10ኛ እና ያሉትን ደረጃዎች ይዘዋል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top