Connect with us

ላዳ ታክሲዎች ከአገልግሎት በጡረታ ሊሰናበቱ ነው

ላዳ ታክሲዎች ከአገልግሎት በጡረታ ሊሰናበቱ ነው
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

ላዳ ታክሲዎች ከአገልግሎት በጡረታ ሊሰናበቱ ነው

በአዲስ አበባ የሚገኙ የቆዩ ላዳ ታክሲዎች በአዳዲስ ታክሲዎች እንዲተኩ እንደሚደረግ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተናገሩ። ለዚህም የታክሲ ባለቤቶችን ከባንክ ጋር የማስትሳሰር ስራ እንደሚሰራም ኢ/ር ታከለ ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ የታክሲና የሀይገር ባስ ማህበራት ለተገልጋዩ ክብርን በመስጠት ለማገልገል የሚያስችል መርሐ ግብር ይፋ ማድረጊያ መድረክ ተከናወናል።

በመርሀ ግብሩ ላይ 13 የታክሲ እና ሶስት የሀይገር ባስ ማህበራት ተሳትፈዋል።

መርሐ ግብሩ በተለይ ለአረጋውያን፣ ለነፍሰጡሮች እና ለአካል ጉዳተኞች በተሻለ መንገድ ለማገልገል የሚያግዝ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት ኢ/ር ታከለ ኡማ አነስተኛ ታክሲዎችና ሀይገር ባሶች ለነዋሪው እየሰጡ ላሉት አገልግሎት አመስግነዋል።

የታክሲ ባለንብረቶች በተለያዩ ጊዜያት ለሚያነሱዋቸው ጥያቄዎች አስተዳደሩ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑንን ተናግረዋል ኢ/ር ታከለ።

በእድሜ ያረጁ አነስተኛ ታክሲዎች አዳዲስና የመጫን እቅማቸው ከፍ ባሉ አነስተኛ ታክሲዎች እንዲተኩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናግረዋል ኢ/ር ታከለ።

ለዚህም ባለንብረቶችን ከባንክ ጋር የማስተሳሰር ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የታክሲና የሀይገር ባስ ባለንብረቶች በበኩላቸው የከተማ አስተዳደሩ በሚያከናውናቸው ሁሉን አቀፍ እንቅስቃሴዎች ላይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።(ምንጭ፡-ከንቲባ ጽ/ቤት

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top