Connect with us

የሩስያ ላሞች ከጭንቀት እንዲገላገሉ ‘ቪአር’ ተገጥሞላቸዋል

የሩስያ ላሞች ከጭንቀት እንዲገላገሉ 'ቪአር' ተገጥሞላቸዋል
Photo: Facebook

አስገራሚ

የሩስያ ላሞች ከጭንቀት እንዲገላገሉ ‘ቪአር’ ተገጥሞላቸዋል

አንድ የሩስያ ግብርና ድርጅት ወተት አምራች ላሞቹ ከጭንቀት እንዲገላገሉ ‘ቨርችዋል ሪያሊቲ’ የተሰኘ ቴክኖሎጂ ግንባራቸው ላይ ገጥሞላቸዋል።

አርብቶ አደሩ ድርጅት ለላሞች ተብለው የተዘጋጁ ‘ቪአሮችን’ ነው ላሞቹ ግንባር ላይ የገጠመው።

‘ቪአር’ የተሰኘው ዓይን ላይ የሚደገን መሣሪያ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን በ360 ድግሪ በማሳየት እውነተኛ እስኪመስሉ ድረስ ያደናግራል።

ላሞቹ የተገጠመላቸው ቪድዮ የክረምት ሽታ ያለው ያማረ መስክ ነው ተብሏል።

የሩስያ ግብርናና ምግብ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት፤ አንድ ያስጠናሁት ጥናት ላሞች የሚሰጡት ወተት መጠንና ያሉበት ስሜት (ሙድ) ተያያዥነት እንዳለው ያሳያል ይላል።

የቪአር ቴክኖሎጂ ግንባራቸው ላይ የተሰካላቸው የመጀመሪያዎቹ ላሞች ‘ደስተኛ ቀን አሳልፈዋል፤ ጥሩ የወተት ምርትም ሰጥተዋል’ ተብሏል።

ሚኒስትር መሥሪያ ቤቱ የለቀቀው መግለጫ እንዳመላከተው፤ የሙከራ ትግበራውን ያከናወነው ሞስኮ ጥግ ላይ ያለ አንድ የእንስሳት ተዋፅዖ አምራች ድርጅት ነው።

“በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ያደረግነው ሙከራ እንደሚያሳየው ላሞች በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ሲሆኑ፤ የሚሰጡት ወተት መጠንና ጥራት ይጨምራል” ይላል መግለጫው።

የሙከራ ትግበራውን ተከትሎ አጥኚዎች የቴክኖሎጂውን የረዥም ጊዜ ጥቅምና እና ጉዳት ይመረምራሉ። ውጤቱ አመርቂ ከሆነ የሩስያ ላሞች ግንባራቸው ላይ ቴሌቪዥን ሰቅለው ሊውሉ መሆኑን የዘገበው BBC አማርኛው ነው።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top