Connect with us

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ
Photo: Facebook

ወንጀል ነክ

ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አደረጉ

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፍሬህወት አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል። ኢንጂነር ታከለ በስፍራው የተገኙት በትናንትናው እለት በተማሪዎች ላይ የማስመለስና የሳል ምልክት ታይቷል መባሉን ተከትሎ ነው።

በምልከታቸውም የሆስፒታል የምርመራ ውጤትን ጠቅሰው በተማሪዎች ላይ ከምግብ ጋር የተያያዘ ችግር አለመከሰቱን አስታውቀዋል።

የምግብ መመረዝ አለመከሰቱን ያነሱት ከንቲባው በትምህርት ቤቶች የሚደረገው የምገባ ፕሮግራም በተጠናከረና ተቋማዊ በሆነ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል።

አያይዘውም ፕሮግራሙ በሕግ ደረጃ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ሆኖ ይፀድቃል ማለታቸውን ከምክትል ከንቲባው የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

(ምንጭ፡- ኤፍ ቢ ሲ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top