Connect with us

አንድ ዛምቢያዊ አውሮፕላን አብራሪ የውሽንፍር ጉዳት የደረሰበትን አውሮፕላን በሰላም አሳረፈ

አንድ ዛምቢያዊ አውሮፕላን አብራሪ የውሽንፍር ጉዳት የደረሰበትን አውሮፕላን በሰላም አሳረፈ
Photo: Facebook

አስገራሚ

አንድ ዛምቢያዊ አውሮፕላን አብራሪ የውሽንፍር ጉዳት የደረሰበትን አውሮፕላን በሰላም አሳረፈ

አንድ ዛምቢያዊ አውሮፕላን አብራሪ ሰኞ ዕለት 41 መንገደኞችን የያዘ ዳሽ 8-300 አውሮፕላን ይዞ ሲጓዝ በውሽንፍር ምናልባትም በመብረቅ ቢመታም አደጋ ሳይደርስበት በሰላም ማሳረፉ ተገለጸ።

ፕሮፍላይት የተሰኘው የአገር ውስጥ አየር መንገድ አውሮፕላን ጉዳቱ ሲደርስበት ከቱሪስት ከተማዋ ሊቪንግስተን ወደ ዋና ከተማዋ ሉሳካ እየተቃረበ እንደነበር ተገልጿል።

አውሮፕላኑ አፍንጫው ላይ የውሽንፍር ጉዳት ያጋጠመው ከባሕር ጠለል በላይ 5791 ሜትር (19 ሺህ ጫማ) ከፍታ ላይ እንደነበረም ታውቋል።

ነገር ግን አብራሪው አውሮፕላኑን ኬኔዝ ካውንዳ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ማሳረፍ መቻሉ ተገልጿል።

የፕሮፍላይት ኩባንያ ከፍተኛ አመራር የሆኑት ፊል ሌምባ ሁሉም መንገደኞች በሰላም ማረፋቸውን ገልጸዋል።

“41 መንገደኞችን ያሳፈረው አውሮፕላናችን ከቀኑ 9:20 ገደማ ወደ ሉሳካ ሲቃረብ በመብረቅ ተመትቷል፤ ነገር ግን በአውሮፕላኑ ዲዛይን የተነሣ ብዙም ጉዳት አልደረሰበትም። ይህም የሆነው አውሮፕላኑ የመብረቅ አደጋ ሲደርስበት መከላከል የሚያስችል ቋሚ አካል ያለው በመሆኑ ነው” ሲሉ ሌምባ ለዴይሊ ሜይል ተናግረዋል።

አየር መንገዱ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ የውሽንፍሩ አደጋ ከፍተኛ መሆኑንም አስታውቋል።

አያይዞም ምናልባትም በመብረቅ የመመታት “ሁኔታ” ነበር፤ ነገር ግን ይህ የሚረጋገጠው በአውሮፕላኑ ላይ የቅርብ ፍተሻ ከተካሔደ በኋላ የሚታወቅ ነው ብሏል።

በዚህም የተነሣ አውሮፕላን አብራሪው ሙገሳ ተችሮታል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top