Connect with us

በሩዋንዳ በ5 ወር የተወለዱት መንትዮች በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ

በሩዋንዳ በ5 ወር የተወለዱት መንትዮች በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ
Photo: Facebook

አስገራሚ

በሩዋንዳ በ5 ወር የተወለዱት መንትዮች በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ

በሩዋንዳ ባለፈው ሃምሌ ወር ላይ መደበኛ የጽንሰት ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ባልተለመደ ሁኔታ በ5 ወራቸው የተወለዱት መንትዮች፤ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ኦል አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡

በተረገዙ በ24 ሳምንታቸው በቅርቡ ኪጋሊ ውስጥ በሚገኘው ኪንግ ፈይሰል ሆስፒታል የተወለዱት እነዚሁ ሴትና ወንድ መንትዮች፣ ምንም እንኳን ሲወለዱ ክብደታቸው እጅግ አነስተኛ ቢሆንም፣ ያለ አንዳች የጤና ችግር እንደሚገኙ ዘገባው አመልክቷል፡፡

በተወለዱበት ጊዜ ወንዱ 660 ግራም፣ ሴቷ 620 ግራም ክብደት እንደነበራቸው ያስታወሰው ዘገባው፤ ትክክለኛው ክብደት ግን ከ2600 ግራም እስከ 4500 ግራም እንደሆነና በዚህ አነስተኛ ክብደት የተወለዱት መንትዮቹ በህይወት መቀጠላቸው እንዳስደነቃቸው የሆስፒታሉ ሃኪሞች በግርምት መናገራቸውን አመልክቷል፡፡

መንትዮቹ ያለ ጊዜያቸው ሊወለዱ የቻሉት እናታቸው ከፍተኛ የሆነ የደም ግፊት ስለተፈጠረባት መሆኑን የተናገሩት ሃኪሞቹ፤ ህጻናቱ ያለ ጊዜያቸው መወለዳቸው አስጊ በመሆኑ በልዩ ክፍል ክትትል ሲደረግላቸው እንደቆየና በአሁኑ ወቅትም በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

መንትዮቹ ከተወለዱ ሶስት ወራት ያህል እንደሆናቸውና ወንዱ 2 ኪሎ ግራም ከ90 ግራም፣ ሴቷ አንድ ኪሎ ግራም ከ500 ግራም ክብደት እንዳላቸው፤ እድገታቸውም ጥሩ የሚባል እንደሆነም ዘገባው አክሎ ገልጧል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top