Connect with us

“ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን” በሚል መሪ ቃል ባህር ዳር የመጻሕፍትና የንባብ ባህል ድግስ ላይ ናት

"ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን" በሚል መሪ ቃል ባህር ዳር የመጻሕፍትና የንባብ ባህል ድግስ ላይ ናት፡፡

ወንጀል ነክ

“ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን” በሚል መሪ ቃል ባህር ዳር የመጻሕፍትና የንባብ ባህል ድግስ ላይ ናት

“ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን” በሚል መሪ ቃል ባህር ዳር የመጻሕፍትና የንባብ ባህል ድግስ ላይ ናት፡፡
****
ህዳር ሲታጠን መጽሐፍ ሲተነተን በሚል መሪ ቃል በብሔራዊ ቤተ መጻሕፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ መሪነት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲና በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አጋርነት ባህር ዳር ከተማ የንባብ ባህል እና የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ድግስ ላይ ናት፡፡

አርብ ህዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም. የጀመረው ይህ ኩነት በተለያዩ ዝግጅቶች መከበሩን ቀጥሏል፡፡ በመክፈቻው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፔዳ ካምፓስ በንባብ ባህል ዙሪያ ያተኮረ የፓናል ውይይት ተካሂዷል፡፡

ህዳር 13 ቀን ቅዳሜ ጠዋት ደግሞ በጣና ሐይቅ ዳርቻ የተዘጋጀው የመጻሕፍት አውደ ርዕይና ባዛር በአማራ ክልል ፖሊስ ማርሽ ባንድ የጎዳና ላይ ቅስቀሳ ታጅቦ በድምቀት ተከፍቷል፡፡ እሁድ ባህር ዳር አንጋፋና ወጣት ደራሲዎች ልምዳቸውን ያካፈሉበት የንባብ ባህል ንቅናቄን ያካተተ የሥነ ጽሑፍ ምሽት አካሂዳለች፡፡

ዛሬ የቀጠለው ይህ የንባብ ባህል ዘመቻ ንቅናቄ በፓፒረስና ዋተር ፍሮንት ሆቴሎች በአርካይቭና በህጻናት ንባብ ላይ ያተኮሩ የፓናል ውይይቶች እያስተናገደ ሲሆን ከሰዓት በኋላ ደግሞ በባህር ዳር ማረሚያ ቤት በተመሳሳይ መልኩ የንባብ ባህልን የሚያግዝ ኩነት ተዘጋጅቷል፡፡

እስከ ነገ የሚቀጥለው ይህ ኩነት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ መጻህፍትና ቤተ መዛግብት ኤጀንሲ በተለያዩ ክልሎች የሚያዘጋጃቸው መደበኛ የንባብ ባህል ንቅናቄ ኩነቶች አካል መሆኑን ከአዘጋጆቹ ለመረዳት ችለናል፡፡

Click to comment

More in ወንጀል ነክ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top