Connect with us

የቢሮ ሕንፃው ያሰጋቸው ሄልሜት አጥልቀው የሚሰሩ ህንዶች

የቢሮ ሕንፃው ያሰጋቸው ሄልሜት አጥልቀው የሚሰሩ ህንዶች
Photo: Facebook

አስገራሚ

የቢሮ ሕንፃው ያሰጋቸው ሄልሜት አጥልቀው የሚሰሩ ህንዶች

መንግሥት ከህዝብ ከሚሰበስበው ግብር የዜጎችን መሠረታዊ ፍላጎት ማሟላቱ ግድ ነው፡፡ ቢሮ ውስጥ ቁጭ ብለው የመንግሥት የዕለት ተዕለት ሥራ እየሠሩ ደግሞ በአለቆቻቸው ችላ ከተባሉ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር አለ ማለት ነው፡፡ ወይም አመራሩ ምንዝሩን (የበታቹን ሠራተኛ) በማማረር አልያም አለቃው በመደናበር ግዴታውን ያለመወጣቱ ማሳያ ነው፡፡ ሕንፃቸው እያሰጋቸው መሆኑን ለመንግሥትና ለመገናኛ ብዙኃን ተደጋጋሚ አቤቱታ ሲያቀርቡ የነበሩ ህንዳውያን ተሰላችተው ‹‹ለቢሮ ሥራቸው ሄልሜት አጥልቀው መሥራት ጀመሩ፡፡›› ይለናል የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ፡፡ በግሌ የአለቆችን ቸልተኝነት ብንቅም የህንዳውያን ምንዝሮች ሥራን ግን አደንቃለሁ፡፡ እኛ ብንሆን ኖሮ ሕንፃ ለመደርመስና ሕይወት ለማፍሰስ እንሮጥ ነበር፡፡ ህንዳውያኑ ሀገራቸውን ስለሚወዱ መንግሥት ቢሮክራሲ በማብዛት ችላ ቢላቸውም ለሀገራቸው ለመሥራት ግን አልቦዘኑም፤ ሀገራቸውንም ችላ አላሉም፡፡

በህንድ ኡተር ፓራዳሽ ግዛት ባንዳ ከተማ የሚገኙ እነዚህ የመንግሥት ሠራተኞች የሞተር ሳይክል ሄልሜት (የራስ ቅልን ከአደጋ መከላከያ) አጥልቀው የቢሮ ሥራ እየሠሩ በቅርቡ በማኅበራዊ ድረ ገፅ የብዙዎችን ትኩረት ስበው ነበር፡፡ ምናልባት የሕንፃው ጣራ በላያቸው ላይ ሊራገፍ ቢችል ተብሎ መሆኑን የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ አስረድቷል፡፡ በከተማው የኤሌክትሪክ ክፍል ቅጥር ሠራተኞች ትልልቅ የሞተር ሳይክል ሄልሜት ለጭንቅላታቸው አጥልቀው ቢሯቸው ሲሠሩ የሚያሳዩ ፎቶዎችን ማኅበራዊ ትስስር ገፆችና የህንድ ዜና አገልግሎት ተጋርተውታል፡፡

አብዛኛዎቹ ምንጮች የመንግሥት ተቀጣሪዎቹ የሞተር ሳይክሎች ደጋፊ ወይም አቃፊ አይደሉም። ቀስ በቀስ እየተፈረካከሰ ያለው ጣራ ግን እንዳይጎዳቸው ጭንቅላታቸውን ለመከላከል ሊሆን ይችላል፡፡ ከዓመታት በፊት ለሪፖርተሮች የጽህፈት ቤቱ ሕንፃ እንደሚያሰጋቸው ቢናገሩም ማንም መፍትሔ የሚሰጥ አልተገኘም፡፡ እናም የራስ ቅላቸውን ከአደጋ ሊከላከል የሚችለውን ሄልሜት አጥልቀው ወደ ቢሮ እየገቡ ለመሥራት ወስነው ተገበሩት፡፡

‹‹ይህን መሰል ሁኔታ ያጋጠመን እኔ ከተቀላቀልኩ ከሁለት ዓመት በፊት ነው፡፡ ለባለሥልጣኖች ጽፈን ነበር ግን ጆሮ ዳባ ልበስ አሉን፡፡›› ሲሉ ከተቀጣሪዎች መካከል ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ግለሰብ ለህንድ ዜና አገልግሎት ተናግረዋል፡፡

የዛሬይቱ ህንድ የተባለ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ የጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች አንዲት ስንስዝር ያጋነኑት ነገር የለም፡፡ በቤቱ መካከል ጣራው እንዳይፈረካከስ የሚረዳ ምሰሶ ወይም አምድ ቢኖረውም ጣራዎቹ በቀዳዳዎች የተሞሉ ናቸው፡፡

የሚገርመው በህንድ ቢሮዎች የሞተር ሳይክል ሄልሜት አጥልቀው የሚገቡ ሠራተኞች በዜና ሲዘገብ የመጀመሪያው አይደለም፡፡ እኤአ ከ2017 ወዲህ በተሰነጣጠቀ የመንግሥት ሕንፃ ውስጥ ስለሚሠሩ ሠራተኞች ቢሀር በሚባል አካባቢ በተመሳሳይ መልኩ የቢሮ ሥራቸውን ለመሥራት በስጋት ሄልሜት ለማጥለቅ እንደተገደዱ ተዘግቦ እንደነበር የኦዲቲ ሴንተራል ዘገባ ያመለክታል፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top