Connect with us

ኢትዮጵያ ፀረ ሽብር ሕጉን «አለአግባብ» መጠቀም ቀጥላለች ሲል አምነስቲ ተቸ

ኢትዮጵያ ፀረ ሽብር ሕጉን «አለአግባብ» መጠቀም ቀጥላለች ሲል አምነስቲ ተቸ
Photo: Amnesty International

ህግና ስርዓት

ኢትዮጵያ ፀረ ሽብር ሕጉን «አለአግባብ» መጠቀም ቀጥላለች ሲል አምነስቲ ተቸ

በሽብር ተጠርጥረው ለወራት ከታሰሩ በኋላ ክስ ሳይመሠረትባቸው 22 የመንግሥት ተቺዎች መለቀቃቸው የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ፀረ ሽብር ሕጉን አላግባብ መጠቀም መቀጠላቸውን ያመለክታል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ተቸ።

ከትናንት በስቲያ ከቀትር በኋላ የተለቀቁት 22 ታሳሪዎች በሰኔ 15ቱ የከፍተኛ የፖለቲካ እና የጦር ኃይል ባለሥልጣናት ግድያ በኋላ ከተያዙት ከ200 የሚበልጡ ዜጎች መካከል መሆናቸውንም አምነስቲ ትናንት ባለወጣው መግለጫ ጠቁሟል። ከታሳሪዎቹ አብዛኛዎቹም በይፋ ምንም አይነት ክስ ሳይመሠረትባቸው እንዲሁ መለቀቃቸውንም አመልክቷል።

በዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት የኢትዮጵያ ጉዳይ ተመራማሪ አቶ ፍሰሀ ተክሌ፤ ከወራት በኋላ ያለምንም ክስ ትናንት 22ቱ ተጠርጣሪዎች መለቀቃቸው፤ የመንግሥት ባለሥልጣናት ተቺዎችን በዘፈቀደ ለማሰር ፀረ ሽብር ሕጉን አለአግባብ መጠቀም የመቀጠላቸው ውጤት ነው ብለዋል።

«ለረጅም ጊዜ እስር ላይ ነበሩ ፍርድ ሳይቀርቡ፤ ማስረጃ በሌለበት ሁኔታ ነው ታስረው የነበሩት፤ በምን ምክንያት እንደተጠረጠሩም ግልፅ አይደለም። ምን አርገዋል ተብሎ ባልታወቀበት ሁኔታ ነበር ታስረው የቆዩት። እናም በስተመጨረሻ እንግዲህ አራት ወር ሲያልቅ ነው ትናንት በመታወቂያ ዋስ አብዛኞቹ የተለቀቁት። ይህ የሚያሳየው ምንድነው የፀረ ሽብር አዋጁ ላይ ያሉት ክፍተቶች ትችት የሚያቀርቡ ሰዎችን ለማጥቃት እየዋለ መሆኑን እና ያም ደግሞ እንደቀጠለ፤ በፊትም ይደረግ ነበረ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሥልጣን ላይ ከመምጣታቸው በፊት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በዚህ አዋጅ ሰለባ ነበሩ፤ እሱ ይቀራል በተባለበት በአሁኑ ጊዜ ደግሞ እንደገና ይህ ሕግ እንደ አዲስ እየተተገበረ ነው።» በዚህ አሻሚ እና ከሚገባው በላይ በተለጠጠው ሕግ አማካኝነትም በርካቶች አሁንም በየእስር ቤቱ እየተንገላቱ መሆናቸውንም ተመራማሪው ገልጸዋል። አምነስቲ ኢንተርናሽናል የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት የፀረ ሽብር ሕጉን ከዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት አኳያ የማሻሻል ሥራን እንዲያፋጥኑ ጠይቋል።

DW

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top