Connect with us

አቢይ አህመድና ለማ መገርሳ ከመታመን ማማ ላይ ወደቁ

ህግና ስርዓት

አቢይ አህመድና ለማ መገርሳ ከመታመን ማማ ላይ ወደቁ

አቢይ አህመድና ለማ መገርሳ ከመታመን ማማ ላይ ወደቁ | ትርጉም ዶክተር አብርሃም አለሙ

አቢይና ለማ መገርሳ የሀረርና አካባቢውን ኦሮሞ ሰብስበው ስለ “ሰላም” ሲሰብኩ፣ ከተስብሳቢው መካከል፥ “ከሰሞኑ በወንድማችን ጀዋር መሀመድ ላይ በተቃጣው የህይወት ማጥፋት ሙከራ የአቢይ አህመድ እጅ አለበት መባሉ እውነት ነው ወይ?” የሚል ጥያቄ ተነስቶ የሰጡት ምላሽ፣ ሁለቱ ነባር ካድሬዎች ጨርሶ ለሀገርም፣ ለህዝብም የማይታመኑ፣ የፈጠራቸውን አምላክም የማይፈሩ አፈ-ቅቤዎች ለመሆናቸው ጥሩ ማሳያ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ በጠቅላላ ይህንኑ በራሱ የአእምሮ ሚዛን መዝኖ መፍረድ ይችል ዘንድ፣ በኦሮሚኛ የተናገሩትን ወደ አማርኛ ቃል በቃል እንደሚከተለው ተርጉሜዋለሁ (ለትርጉሙ ትክክለኛነት ጥያቄ የሚያነሳ ቢኖር፣ ሙሉ ሃላፊነቱን እወስዳለሁ፤ መልስ እሰጣለሁ)።

የለማ መገርሳ ምላሽ

ሰሞኑን ሆነ እየተባለ ያለው፣ ፖሊሶች በሌሊት ሄደው ጠባቂዎቹን (የጀዋር መሀመደን) አነሱ ማለትን ሰምተን፣ ሁላችንም አዝነናል። ይሄ ድርጊት ባስቸኳይ አንዲታገድለት መደረግ አለበት ብለን ሁላችንም ተቃውመን፣ ይህን ድርጊት የፈጸሙትም በህግ መጠየቅ አለባቸው ብለን በጥብቅ እናምናለን። በዚህ ጉዳይ ላይ ህዝቡ ማወቅ ያለበት፣ ወንድማችንን ማጥፋት ብንፈልግ ወደዚህ ሀገር እንዲመጣም አንጋብዘውም ነበር። እንዲያውም እንኳንስ እሱን ቀርቶ ሌሎችን ታስረው የነበሩትንም ስንለቃቸው ቆይተን የለም ወይ። እሱን ማጥፋት ብንፈልግ ለሱ ጠባቂ መድበን አንጠብቀውም ነበር። ባንጻሩ የዚህ ታጋይ ህይወት በማይረባ ሰው እጅ እንዳይጠፋ ብለን ነው ስንጠብቀው የቆየነው። ስለሆነም አሁንም የተፈጸመበት ነገር ተቀባይነት የለውም፤ እንቃወማለን። ነገም አብረን እንሰራለን፤ አብረን እንታገላለን።

የአቢይ አህመድ ምላሽ፥-

“ጀዋርን በግልጽ ከመጀመሪያው አንስቶ እስከ ዛሬ እየጠበቀው ያለው መንግስት ነው። እናንተ ጥበቃ መድቡለት ብላችሁ መቼ ጠየቃችሁን? መጠበቅ አለበት ብላችሁ ጠይቃችሁናል?

“አልጠየቅንም።”

ጀዋርስ ጥበቃ ያስፈልገኛል ብሎ ጠይቆናል? እኛው ነንኮ እየጠበቅነው ያለነው። ለምንድን ነው በዚህ በማይሆን መንገድ ልንወቃቀስ ያስፈለገን? እኛ ነን ጉዳት ሊደርስበት ይችላል ብለን፣ ከመጀመሪያው ወደዚህ ከገባበት ጀምሮ እየጠበቅነው ያለነው እኛ ነን። መጠበቅም ብቻ አይደለም፤ ከዚያም የበለጠ. . .ብዙ ነገር ማንሳት ይቻላል።

አንድ የተፈጠረ ስህተት አለ፤ ሰምቻለሁ። በፓርላማ ንግግር ባደረግሁበት ጊዜ የሆነ አባባል ተጠቅሜ ነበር “ስኮርት ሀገር ያላችሁ” ፤ ብየ ነበር፤ ካስታወሳችሁ:: ስኮርት በሀገራችን፣ ጅማ መጠባበቂያ 5ኛ ጎማ ማለት ነው ፤ ታውቁታላችሁ አይደል? እዚህም[ሐረር] እንደሱ ነው አይደል? ለካስ በነጃዋር ሀገር ስኮርት ማለት ጥበቃ ማለት ነው (ሳቅ እያለ):: እሱ የመሰለው “ጥበቃ ያላችሁ ሰዎች” ብሎ ነው የተረዳው (ሳቅ እያለ) ፤ እየሰማችሁኝ ነው? ሆኖም እንደዚህ እንኳን ቢባልስ? (ተሰብሳቢው በ”አልገባንም” ተንጫጫ)

“አልገባችሁም?”

“አዎ” (ተሰብሳቢ)

ፓርላማ ላይ በተናገርሁ ጊዜ፣ “ስኮርት ሀገር ያላችሁ ሰዎች ፤ ” ብዬ ነበር::

“ገባችሁ ?”

“አዎ”

“ስኮርት” ማለት የመኪና ጎማ ሆኖ ፣ ሌላው ጎማ ሲፈነዳ መጠባበቂያ(ትርፍ) ጎማ ማለት ነው:: “ትርፍ ሀገር ያላችሁ፤” ማለቴ ነበር:: በነ ጃዋር ሀገር ግን፣ “ስኮርት” ማለት “የፖሊስ ጥበቃ” ማለት ነው:: እየሰማችሁኝ ነው?

ጥበቃ ያላችሁ ተጠንቀቁ እንዳልኩ አድርጎ ነው እሱ የተረዳው። ይሁን እንጂ በንግግር ሳይሆን በሃሳብም፣ በሃሳብም እናንተ እንደምታስቡት ማሰር፣ መጉዳት፣ መግደል፣ ጀዋርን ቀርቶ ሊገድሉን የተዘጋጁትንም ትተን አብረን እየኖርን ነው ያለነው። ማንን ገድለን እናውቃለን እኛ?

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top