Connect with us

መቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆች ወደሚኖሩበት ክልል ስድስት መቶ ተማሪዎችን አልክም ማለት

መቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆች ወደሚኖሩበት ክልል ስድስት መቶ ተማሪዎችን አልክም ማለት
AFP

አስገራሚ

መቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆች ወደሚኖሩበት ክልል ስድስት መቶ ተማሪዎችን አልክም ማለት

መቶ ሺህ የትግራይ ተወላጆች ወደሚኖሩበት ክልል ስድስት መቶ ተማሪዎችን አልክም ማለት የህወሃት ድግስ ምን ምን እንደሚሸት ማሳያ ነው፤
ኽረ ለመሆኑ አምናና ካቻምና ተመድበው እየተማሩ ያሉትስ?
****
ከሰለሞን ሃይሉ

የህወሃት ሀሳብ እኩይ ነው፡፡ ፖለቲካዊ አቋሟን ባልኮንነውም ትናንት ተፈጥራ የዘመናት ታሪክ በገመዳቸው ህዝቦች ላይ መቆመሯን ግን አፍርበታለሁ፡፡ ዛሬ በአማራ ክልል የትግራይ ተወላጅ የሆኑ መቶ ሺዎች እየኖሩ ነው፡፡ አንዳንድ ቦታ ካቢኔም ናቸው፡፡ አንዳንዱ አካባቢ ግዙፍ ነጋዴ፤ ካህናቱም ብዙ ናቸው፡፡ በዚህ የህዝብ አብሮነት ላይ ቀረኝ የሚለውን የክፋት ሚሳኤል መተኮስ የሚፈልገው ህወሃት ግን ዘንድሮ አማራ ክልል የደረሳቸውን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አልክም ብሏል፡፡

ሀሳቡን የትግራይ ህዝብ እንዴት እንደሚመለከተው አላውቅም፤ ግን የህወሃት የነገር ረሃብ ማሳያ መሆኑን ለመረዳት ይቸገራል ብዬ አላስብም፤ ዜጎች እንኳን በሀገራቸው ለአራት አመት ቆይታ ለመኖር የሚከለክላቸው አንዳች ህዝባዊ ስነ ልቦና የለም፤ ፖለቲካውን ደግሞ አብሮ መታገል ነው፡፡

የአማራ ህዝብ ዛሬም አክሱም ጽዩን ደብሩ ናት፤ ለምሳሌ በማርቆስ፣ በጎንደር እና በባህር ዳር በቀጣዩ ህዳር ወደ አክሱም መሄድ ለሚፈልጉ ምዕመናን መዝሙር ቤቶችና የጉዞ ማህበራት ምዝገባ እያካሄዱ ነው፡፡ የሚመሩትን ህዝብ የማያውቁ ግን ዳርና ዳር ቆመው ከዛሬ ነገ ጦርነት ይወርዳል በሚል የደም መጠጣት ሱሳቸው እያዛጋቸው ነው፡፡

ከትግራይ ወደ አማራ ክልል እንኳን ዛሬ 2008 እና 2009 ዓ.ም. ተማሪ ተምሮ ወደ ቀዬው ሄዷል፡፡ የነበሩት ችግሮች ደግሞ አክሱምና አዲግራት ወለጋና ቡሌ ሆራ ከነበረው የተለየ አልነበረም፡፡ አሁንም ቢሆን በአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች አምናና ካቻምና የተመደቡ የትግራይ ተማሪዎች አሉ፡፡ እነሱን እንኳን ማሳብ ሳይፈልግ የፖለቲካ ቁማር ለመጫወት መሞከር ቢያስገርምም ብርቅ ግን አይደለም፡፡

በዚህ አጋጣሚ ደጋግሞ ማሰብ ሁለት አንድ ህዝብ በእስተርጅና ስልጣን ላይ ለመቆየት እናባለው ብሎ ማሰብ መጨረሻ ውጤቱ በዚህ ሲጋመድ ሲዋለድ በኖረ ህዝብ መበላት መሆኑን ሳንጠቁምም ሳናስረዳም አናልፍም፡፡

አንዲት የአማራ እናት የትግራይ ልጅን ከአማራ ልጅ የምትለይበት ሥነ ልቦና ምን እንደሆነ አላውቅም፤ እንደማይኖር እና ልዩነቱ እንደማይገባት ግን አምናለሁ፡፡ እንኳን የትግራይ ልጅ ህወሃትን እንኳን ከእኛ መነጠል አቅቶን ነው እኮ ለዘመናት ስንሰቃይ የኖርነው፤ እናም ደጋግሞ ማሰቡ አይከፋም፡፡ በዚህ አጋጣሚ ግን ሀሳቡ የህወሃት ድግስ ምን ምን እንደሚሸት ማሳያ ነው፡፡

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
1 Comment

More in አስገራሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top