Connect with us

በዶክተር አረጋዊ በርሄ የተዘጋጀ “የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ” የተሰኘ መፅሃፍ ሊመረቅ ነው

በዶክተር አረጋዊ በርሄ የተዘጋጀ "የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ" የተሰኘ መፅሃፍ ሊመረቅ ነው
Ethiopian News Agency

ዜና

በዶክተር አረጋዊ በርሄ የተዘጋጀ “የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ” የተሰኘ መፅሃፍ ሊመረቅ ነው

በዶክተር አረጋዊ በርሄ የተዘጋጀ “የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ” የተሰኘ መፅሃፍ ሊመረቅ ነው

ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ ከህወሃት ትግልና የፖለቲካ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘን ታሪክ የሚዳስስ  “የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ” የተሰኘ የዶክተር አረጋዊ በርሄ መፅሃፍ በመጪው እሁድ ይመረቃል፡፡

መፅሃፉ ከ1967 ዓ.ም ጀምሮ ያለውን የፖለቲካ እንቅስቃሴና የግጭት መንስኤዎችን በመቃኘት ከምክንያታቸው በመነሳት ሃሳባዊ የመፍትሄ ትንታኔ ማስቀመጡን የመፅሃፉ አዘጋጅ ዶክተር አረጋዊ በርሄ ለኢዜአ ገልፀዋል።

“የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ፖለቲካዊ ታሪክ” የተሰኘው ይህ መፅሃፍ 450 ገፆች ያሉት ሲሆን ከአሁን ቀደም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ለአንባቢያን  ደርሷል፡፡

መፅሃፉ በአማርኛ ተተርጉሞና ወቅታዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታክሎበት እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም ለምረቃ ይበቃል ተብሏል።

ህወሃት የብሄር ትግል ለምን ጀመረ? ትግሉ እንዴት ተጀመረ? ህወሃትን ለስልጣን ያበቃው ምንድነው? የሚሉትን ጭብጦች በስፋትና በጥልቀት የሚተነትን  መሆኑም ተገልጿል።

ይሁን እንጂ መጽሃፉ በዋናነት የሚፈልገው የኢትዮጵያን የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ችግሮች፣ የብሄር ግጭቶችና መንስኤያቸውን በትረካና በሃሳባዊ ትንታኔ መልዕክት ማስተላለፍ እንደሆነ ዶክተር አረጋዊ ገልጸዋል።

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ የሚታየው ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ብሄር ላይ የተመረኮዘ፣ የኢትዮጵያዊያንን የቀደመ የአብሮነት ታሪክ የረሳና ያልነበረ ታሪክ ያመጣ ነው ሲሉ ፀሃፊው ተናግረዋል።

ይህ የፖለቲካ አካሄድ በተለይ ውስን የተፈጥሮ ሃብት ባላቸውና የስልጣን ሽሚያ በሚታይባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገራት ጉዳቱ የጎላ ነው ሲሉም አክለዋል።

ይህም ዜጎች ሰዋዊ የሆነውን መልካም ስብዕና ትተው ወደ ግጭት እንዲያመሩ እንደሚያደርጋቸው ነው የጠቆሙት።

ዶክተር አረጋዊ ኢትዮጵያዊያን ከጥንት ጀምሮ የተሳሰሩና አብረው የኖሩ ወደፊትም የሚኖሩ ናቸው በማለትም ጠቅሰዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top