Connect with us

ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ  ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ  ለማካሄድ ታስቧል

ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ ለማካሄድ ታስቧል
Ethiopian News Agency

ዜና

ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ  ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ  ለማካሄድ ታስቧል

ስድስተኛውን አገራዊ ምርጫ  ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ  ለማካሄድ ታስቧል

  የመራጮች ምዝገባ  ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት ይካሄዳል፣

ለስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ከታህሳስ እስከ ጥር ባሉት ጊዜያት የመራጮች ምዝገባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ቦርዱ ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ በሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ከሲቪክ እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር እየመከረ ነው።

በምክክር መድረኩ መክፈቻ ላይ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደተናገሩት ከታህሳስ እስከ ጥር ወር 2013 ዓ.ም ለ6ኛው አገራዊ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ይካሄዳል።

 “ከጥር የመጀመሪያው ሳምንት እስከ የካቲት አጋማሽ ደግሞ የእጩዎች ምዝገባ እንዲሁም ከየካቲት አጋማሽ ጀምሮ የምረጡኝ ቅሰቀሳ ይጀመራል” ሲሉም ተናግረዋል።

የስድስተኛው ዙር ምርጫ የድምጽ መስጫ እለት ከግንቦት መጨረሻ እስከ ሰኔ መጀመሪያ ባለው ጊዜ እንደሚሆን የቦርዱ ጊዜያዊ የምርጫ አፈጻጸም ሰሌዳ ተካቷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ እና በምርጫ ሂደት ስለሚወሰዱ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ እርምጃዎችን በተመለከተ ከሲቪክ ማህበራት እና ከመገናኛ ብዙሃን አባላት ጋር በመወያየት ግብዓት ይወሰዳል ተብሏል።

በተጨማሪም ሲቪክ ማህበራት አና መገናኛ ብዙሃንን የሚመለከቱ ዋና ዋና የምርጫ እንቅስቃሴዎች እና ዝግጅቶች ላይ ውይይት እንደሚደረግም ነው የተገለጸው።

እንደ ወይዘሪት ብርቱካን ገለጻ፣ መድረኩ የተዘጋጀው የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን የሚያነሷቸውን ሀሳቦች በመጨረሻ ለሚወጣው የምርጫ ጊዜ ሰለዳ እና የአፈጻጸም ዕቅድ ላይ በግብዓትነት ለመጠቀም ታስቦ ነው።

በመድረኩ በምርጫ ሂደት የሚተገበሩ የኮቪድ-19 የጥንቃቄ መመሪያ መነሻ ሀሳቦች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል።

በተጨማሪም ዋና ዋና የምርጫ ተግባራት በሚተገበሩበት ጊዜ የሲቪክ ማህበራት እና የመገናኛ ብዙሃን ያላቸውን ሚና የተመለከቱና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።(ኢዜአ፣ አዲስ ማለዳ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top