Connect with us

የአዲስ አበቤዉ ፍርሀት  

የአዲስ አበቤዉ ፍርሀት
Tamrat Getachew/ The Reporter

ነፃ ሃሳብ

የአዲስ አበቤዉ ፍርሀት  

የአዲስ አበቤዉ ፍርሀት  

በያሬድ ነጋሽ

“ተጓዝ ነገር ግን ፍርሀት በሚነዳህ መንገድ አትጓዝ” ይላሉ ፈላስፎች  ምክንያቱም ፍርሀት ጭንቀትን : ጭንቀትም በቅጡ ማሰብ እንዳንችል ይገታንና ካሰብንበት ለመድረስ የአርባ ቀኑ መንገድ ወደ ፍሬ አልባ የአመታት ጉዞ ስለሚቀየር ነዉ :: 

የአዲስ አበባ ወጣት የዚህ ፍርሀት የሞላበት ጉዞ ሰለባ ሆኖ ይታየኛል::በተለይም ከተማዋ ላይ ተወልዶ ያደገው ወጣት :: በከተማዋ እየተከወኑ ያሉ ነገሮች ሁሉ ፍርሀት ውስጥ ይከቱታል :: 

ተወልዶ ባደገባት ከተማዉ የባለቤትነት ጥያቄዉ ተከደኖ ይብሰል የተባለ ጉዳይ ነውና የመፈናቀልና ሀብት ንብረቱን የመነጠቅ ስጋት ያንዣብበታል፡፡

በገዛ ከተማው ከስልጣን ገሸሽ የተደረገ ነውና እሱን ባይ ወኪል ያጣ ይመስለዋል:: አንገት ማስገቢያ እንዲሆነው ካለው ላይ ቀንሶ በቋጠራት ጥሪት የገነባው የጋራ መኖሪያ ቤት አንድም በጉልበተኞች በሌላ በኩል ደግሞ በመንግስት አካላት ሲባክን ያይና ነገ ላይ ጎጆ ቀልሶ የመኖር ህልሙ ውስብስብ ይልበታል::

ብሄሬ የሚለው የሌለው አዲስ አበቤ ነውና ብሄርን መሰረት ካደረገው ስርአት ጋር አለመግባባት ውስጥ ይሰጥማል: :

በ1997 ዓ.ም አፋኝና ጨቋኝ የነበረውን የወያኔ መንግስት ለመገርስ በተቀረው የሀገሪቱ ክፍል የሚኖረው ዜጋ እምብዛው እንቅስቃሴ ባላሳየበት ወቅት አዲስ አበቤው በምርጫ ካርድ አልሆን ቢለው  መሳሪያ ከታጠቀው ሀይል ጋር ባዶ እጁን ፊት ለፊት በመጋፈጥ በርካታ ልጆቹን ሰውቶ ሳለ አሁን የተገኘው ለውጥ ላይ እጁ እንደሌለበት ሲነገረው አመድ አፋሽነት ይሰማዋል ::

የመብት ጥያቄውን ለማቅረብ ሰላማዊ ሰልፍ ይሁን ስብሰባዎች ለማድረግ ፍቃድ ሲከለከል እና ሰልፍ የወጡትም ቢሆኑ ለጥፋት አድራሾች የታጠፈው የፖሊስ ክንድ ጀርባቸው ላይ ሲዘረጋ ይመለከትና በቦንብ ፍንዳታ እስከመሞት የደገፈው አዲሱ መንግስት ወዴት አለ ሲል ይጠይቃል:: በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ስነ-ልቦናውን የሚፈታተኑ ነገሮች በርክተው ይታዩታል::

አንድ ማህበረሰብ በኑሮ ጥራት መመዘኛ (life quality index )መሰረት የማህበረሰቡ ጥሪት የማፍራት ነፃነቱ ( creation of wealth ): ዘላቂነት ባለው ሁኔታ በጤንነት መኖሩ (duration of life in good health ) እና ህይወትን በጥሩ መልኩ አጣጥሞ የሚያልፍበት ምቹ ሁኔታ መኖሩ (available to enjoy life) ከግምት ውስጥ ይገቡና የኑሮዉ ጥራት ጥሩ ወይንም መጥፎ  ተብሎ ይፈረጃል::

ከዚህ መነሻነት አዲስ አበቤውን በፍርሀት ከሚሸነቁጡት ከላይ ካየናቸው የስነ-ልቦና  ጫናዎች አንፃር ሀብት ማፍራት ይሁን ባፈራዉ ሀብት የማዘዝ ነፃነቱ የተገደበ እና ህይወትን ከስጋት ወጥቶ ማጣጣም የተሳነው ከመሆኑ አንፃር በ life quality index መመዘኛ እቺን አጭር እድሜ በጥራት አጣጥሞ የመኖሩ ነገር እጅግ የወረደ ሆኖ እንደሚገኝ አያጠራጥርም :: የዜጋዉ ምርታማነትም እንደዛዉ፡፡

የፍርሀት መንገድ ሌላም መልክ አለው:: ይሄውም ደህንነትን ለማስጠበቅ በሚል ሰበብ በህቡ መደራጀትን ያበረክታል ፡፡ህገ-ወጥ የመሳሪያ ዝውውርን ያስፋፋል :: (ይህ መንገድ ጥፋትን እንደሚጋብዝ ልብ ይለዋል)

እንደዚህ ጽሑፍ ጸሐፊ አስተያየት አዲስ አበቤዉን ከፍርሀት ጥለዉታል ብዬ ያነሳሗቸዉ ነጥቦች በከተማችን በግልፅ የሚታዩ እውነታዎች ቢሆኑም በመንግስት በኩል የተለያየ ፖለቲካዊ ቅባት በመቀባት እየታለፉ ያሉ ነገሮች በመሆናቸዉ ከመንግስት አካል መፍትሄ ይመጣል የሚል ግምቴ አናሳ ነዉ፡፡

ይልቁን አዲስ አበቤዉ ስጋቶቹን ሊቀንስበት የሚችልበትና መንግስትን በሰላማዊ መንገድ መሞገት የሚያስችለዉ ግልጽና ህጋዊ አብሮነት በመፍጠር መደራጀት ይገባዋል እላለሁ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top