Connect with us

ዩኒቨርሲቲው በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ከሚያካሄዳቸው ጥናቶች ያጠናቀቀው 34 በመቶ ነው

ዩኒቨርሲቲው በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ከሚያካሄዳቸው ጥናቶች ያጠናቀቀው 34 በመቶ ነው
Photo: Social media

ዜና

ዩኒቨርሲቲው በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ከሚያካሄዳቸው ጥናቶች ያጠናቀቀው 34 በመቶ ነው

ዩኒቨርሲቲው በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ከሚያካሄዳቸው ጥናቶች ያጠናቀቀው 34 በመቶ ነው
• ለጥናቱ ከተያዘው በጀት 60 ከመቶ ተጠቅሟል

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት ለሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ ለማድረግና ጠቃሚ ግብዓት ሊሆን የሚችል የጥናት ግኝቶችን ለማቅረብ ከያዛቸው ጥናቶች 34 ከመቶ ማጠናቀቁን አስታውቋል። ይሁን እንጂ ለጥናቱ ከያዘው 10 ሚሊየን ብር በጀት ውስጥ ስድስት ሚሊየን ብር ተጠቅሟል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምርምር ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ፈታሂ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳስታወቁት፤ ዩኒቨርሲቲው በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ላይ ጥናት ለማካሄድ ከመደበው 10 ሚሊየን ብር ውስጥ ስድስት ሚሊየን ብር ወጭ አድርጓል።

27 ፕሮጀክቶችን ያቀፉ 34 በመቶ የሚሆኑት የጥናት ውጤቶች ቢጠናቀቁም 66 በመቶ የሚሆኑት ጥናቶች ግን እስካሁን አልተጠናቀቁም። አጠቃላይ ጥናቶችን አድርጎ ለመጨረስ ያልተቻለው በበጀት ማነስ ምክንያት ነው።

ጥናቶቹን በሙሉ ለማጠናቀቅ ያልተቻለው ተመድቦ የነበረው በጀት የመደበኛው በጀት በመሆኑና የበጀት ዓመቱ በመጠናቀቁ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ 66 በመቶ የሚሆኑና በሂደት ላይ ያሉት ጥናቶች በያዝነው በጀት ዓመት አዲስ ውሳኔ እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።

በተለይ በኮቪድ 19 ላይ ያጠነጠኑ የምርምር ሥራዎች መቀጠል አለበት ወይስ የለበትም? ገንዘቡ ይበቃል ወይስ አይበቃም የሚለው ጉዳይ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመነጋገር የሚወሰን እንደሆነም ነው የጠቆሙት።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ፤ በጀቱ ለጥናቶቹ አገልግሎት ላይ እንዲውል ይጠናቀቃል ተብሎ የታሰበው እስከ ሰኔ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ቢሆንም ሙሉ ለሙሉ መጠቀም አልተቻለም። ለጥናቶቹ የሚውለው በጀት በ2012 ዓ.ም በነበረው የዩኒቨርሲቲው የምርምር ገንዘብ ተቀናሽ ተደርጎ እንደታሰበና ጊዜው ወዲያው በማለቁ በታቀደው ልክ መሥራት አልተቻለም።

ዳይሬክተሩ፤ የጥናት ቡድኑ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ባደረገው ጥረት ውስጥ ያለቁት ጥናቶች አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ገልፀው፤ በመከላከል ዙሪያ ሊወሰዱ የሚገቡ መፍትሄዎችን እንዳመላከቱ ጠቁመዋል። በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ላይ ለሚሰሩት ሥራዎች ግብዓት መሆናቸውንም አክለዋል።

አብዛኞቹ ምርመራዎች የሚካሄዱት በመንግሥት የጤና ተቋማት ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የሚፈጠሩትን ጫናዎች ለመቀነስ የግል ጤና ተቋማት ምርመራ እንዲያካሄዱ ጥናቱ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ለአብነት ጠቅሰዋል። ወረርሽኙን በተመለከተ አብዛኛውን ሥራ እየሠራ ላለው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ግብዓት መስጠት እንደተቻለም አመላክተዋል።

ጥናቶቹን አስመልክቶ ዩኒቨርሲቲው ባካሄደው ወርክ ሾፕ ጥናቶቹ ከዓላማቸው አንፃር የተወሰነ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ከመድረኩ የተገኘው ግብረ መልስ ማሳያ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም በተቀሩ ጥናቶች ላይ የሚሳተፉ አጥኚዎች በግላቸውም ቢሆን ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን፤ በጀት ከተወሰነ በኋላ እንዴት ማስቀጠል እንደሚቻል ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ንግግሮች እንደሚደረጉና በዚህ መሠረት ሌሎች ቀሪ ጥናቶች እንደሚጠናቀቁ አስታውቀዋል።

ጥናቱን መሰረት አድርጎ የሚመደብ በጀት ባይኖርም ከመደበኛው የዩኒቨርሲቲ የምርምር በጀት ላይ ተቀናሽ በማድረግ እንደሚሰራም ነው የገለፁት። ውሳኔዎቹ የሚሰጡትም 10 ቀናት በኋላ እንደሆነ ዳይሬክተሩ አመላክተዋል።

አዲስ ዘመን መስከረም 8/2013

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top