Connect with us

በአዲስአበባ የመጪው ዓመት የትምህርት ምዝገባ በነገው ዕለት ይጀመራል

አንድነት ኢንተርናሽናል  እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ትምህርት ቤቶች ታገዱ
Photo: Social media

ዜና

በአዲስአበባ የመጪው ዓመት የትምህርት ምዝገባ በነገው ዕለት ይጀመራል

በአዲስአበባ የመጪው ዓመት የትምህርት ምዝገባ በነገው ዕለት ይጀመራል
~ ትምህርት በመስከረም ወር ስለመጀመሩ የታወቀ ነገር የለም፣

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2013 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ከነገዉ እለት እንደሚጀምር አስታወቀ። ከነገ ነሐሴ 19 ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግ የትምህርት ምዝገባ የሚጀመር መሆኑን ቢሮው ይግለፅ እንጂ የመጪው አመት ትምህርት መቼ እንደሚጀምር የገለፀው ነገር የለም።

ቢሮው አያይዞም እንዳለው የምዝገባ ቀኑ እንደተጠበቀ ሆኖ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ላይ ለሚደረገዉ ምዝገባ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጉ እንዲጠብቁ በማሳሰብ የግል ትምህርት ተቋማት ግን ከነገው እለት ጀምሮ ምዝገባ ማካሄድ እንደሚችሉ አስታውቋል።

የትምህርት ሚኒስቴር ቀደም ሲል የቀጣይ አመት የትምህርት ምዝገባ በያዝነው ነሐሴ ወር መጨረሻ ሳምንት እንደሚጀምር፣ ት/ቤቶች አዲስ የክፍያ ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁ ይታወሳል።

አንዳንድ ወላጆች የኮሮና ወረርሽኝ እንዲህ በተስፋፋበት ጊዜ ትምህርት በመስከረም ወር 2013 ዓ.ም ይጀምራል የሚል ግምት እንደሌላቸው በመጥቀስ ምዝገባ አካሂዱ የሚለው የትምህርት ቢሮ ማስታወቂያ የግል ትምህርት ቤቶች ለመጥቀም እንጂ በኑሮ ውድነትና በገቢ ማነስ ለተጎዳው ህዝብ እንዳልታሰበ ያሳያል ብለዋል።

በሌላ ዜና ተማሪዎች በኮሮና ምክንያት ከሚደርስባቸው ጉዳት ይልቅ ትምህርት ቤት ባለመሄዳቸው የሚደርስባቸው ጉዳት ከፍተኛ ነው ሲሉ የእንግሊዝ ከፍተኛ የህክምና አማካሪ ተናገሩ፡፡

ህፃናት በበሽታው የመሞት እድላቸው ከሌሎች አንፃር ዝቅተኛ ነው ያሉት ፕሮፌሰር ክሪስ ዊቲይ ህፃናቱ ከትምህርት ቤት በመራቃቸው ግን በረጅም ጊዜ ውስጥ ጉዳት ያስከትልባቸዋል ብለዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ ለሚቀጥኩት 9 ወራት የዓለም ስጋት ሊሆን ይችላልም ነው ያሉት፡፡

በርካታ ህፃናት ቤት በመዋላቸው እየተጎዱ ነው ያሉት ፕሮፌሰሩ የአዕምሮና አካላዊ ጉዳት በረጅም ጊዜ ውስጥ ሊገጥማቸው ይችላል የሚል ሰጋታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የሀገሪቱ መንግስት በሁሉም የትምህርት ደረጃ ያሉ ተማሪዎች መስከረም ላይ ሙሉ ለሙሉ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ ብሏል፡፡
በስኮትላንድ ደግሞ ትምህርት ቤቶች መከፈት ጀምረዋል፡፡

በኮቪድ 19 ምክንያት ቤታቸው የዋሉ ህፃናት ትምህርት ቤት ከሚውሉት የበለጠ ተጎጂ ናቸው ብለዋል፡፡

ከስጋት ነፃ አማራጭ የለም ያሉት አማካሪው ወላጆችና መምህራንም የትምህርት ቤቶችን መከፈት ጥቅምና ጉዳት ሊገነዘቡ ይገባል ማለታቸውን ከትምህርት ሚ/ር ድረገፅ ያገኘነው ዜና ይጠቁማል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top