Connect with us

የዮዲት ዓይን የኢማም አህመድ ቀልብ

የዮዲት ዓይን የኢማም አህመድ ቀልብ

መዝናኛ

የዮዲት ዓይን የኢማም አህመድ ቀልብ

የዮዲት ዓይን የኢማም አህመድ ቀልብ፣
የዐጼ ሱሲንዮስ ልብ፣ የኢጣሊያ ምኞት የዶክተር አብይ ራዕይ ያረፈባት ደንቢያ-ጎርጎራ
******
(ተጓዡ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ከሸገር ፕሮጀክት ቀጥሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የልማት ዕቅድ ስፍራዎች አንዷ ስለሆነችው የጣና ሐይቅ ዳርቻዋ ጎርጎራ እንዲህ ይለናል፡፡) l ከሄኖክ ስዩም በድሬቲዩብ

ከአዘዞ በታች ከወረዱ በኋላማ መትረፍ የለም፡፡ ደንቢያ ከብት ያለምዳል እንኳን የሰው ልጅ ተብሎ የለ፡፡ ስለ ጎርጎራ ታምሜያለሁ፡፡ ስለ ጎርጎራ ተክዣለሁ፡፡ ቁጭቴን የጣና ማዕበል ውጦ ያስቀረው መስሎኝ ነበር፤ ለካንስ ቀን ይጠብቅ ኖሯል፡፡

ደንቢያ ምስጢራዊ ምድር ነው፡፡ የዩዲት ዓይን አርፎበት ነበር፤ ከወገራ ተወርውሮ፤ ደግሞ የኢማም አህመድ ቀልብ ወድቆበት ነበር ከአዳል ሲገሰግስ ደርሶ፡፡ አሉ ደግሞ ታላቁ ንጉሥ ሱሲንዮስ ልባቸው ደንቢያ ወደቀ፤ ህንጻቸው ጎርጎራ ቆመ፡፡ ደንቢያ ታሪክ ከፍ አድርጎ የሚገልጻት ቅድመ ጎንደር የሀገር መዲና ኾነች፡፡

ጎርጎራ የጣና ዳርቻ ብቻ አይደለችም፡፡ የአጼ ልብነ ድንግል ዘመን የታሪክ ማዕከል ናት፡፡ የደብረ ሲና መገኛ፡፡ የወፍ ገዳም፤ የብርጊዳ በራፍ፣ የማንዳባ አፋፍ፣ የአንጋራ መነሻ፣ የገሊላ ማዶ፣ የጀበራ መንደርደሪያ፡፡ ጎርጎራ፤

ጣሊያን አዲሷን ጎንደር ጣና ዳር ጎርጎራ ላይ መዝረጋት ፈለገ፡፡ የነጻ አውጪዎቹ ምድር ቅኝ መገዛት እንቢ ሲል ምኞቱ ከሸፈ፡፡ የጓድ ሊቀ መንበር የኮለኔል መንግስቱ ቀልብም ጎርጎራ እንደ ካሌብ ደሴት የባህር ትራንስፖርቱ እንብርት ይሆን ዘንድ ፈቀደ፤

ዛሬ ሌላ ዘመን ነው፡፡ ባለቤት የለውም የተባለው ጸጋ የምስራች ተሰማበት፡፡ ጎርጎራ የዶክተር አብይ ራዕይ አረፈባት፡፡ ጎርጎራ እንደ ሸገር፣ ጎርጎራ እንደ እንጦጦ ለልማት ተመረጠች፡፡ ሊያውም ከጎንደር ተሳስራ፡፡ ሊያውም እንደ ወንጪ፣ ሊያውም እንደ ሴሪ፤ እንደ ኮይሻ እንደ አፍሪቃ ዝኆኖቹ መኖሪያ እንደ ጩርጩራ እንደ ጨበራ፡፡

ደስ ብሎኛል፡፡ የተስፋ መቁረጥ ዝምታ ያረበበት የደንቢያ የጣና ዳርቻ የታለመው እውን ከኾነበት ጣና ተአምር ያስተናግዳል፡፡ ባህር ዳር ከጎንደር ሌላ ትዕይት ይዘረጋል፡፡ ሀገር ደበዘዘ የተባለ መልኳን አስጊጣው ደምቃ ታደምቀናለች፡፡ ጎርጎራ ዛሬም የአበው ጸሎት ትናንትናሽን ነገ ያደርገዋል፤ ይሄንን አምናለሁ፡፡

Click to comment

More in መዝናኛ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top