Connect with us

የትራምፕ አስተዳደር ስለ ህዳሴው ግድብ ዳግም አስተያየት ሰጠ

የትራምፕ አስተዳደር ስለ ህዳሴው ግድብ ዳግም አስተያየት ሰጠ
Photo: Social Media

አለም አቀፍ

የትራምፕ አስተዳደር ስለ ህዳሴው ግድብ ዳግም አስተያየት ሰጠ

የትራምፕ አስተዳደር ስለ ህዳሴው ግድብ ዳግም አስተያየት ሰጠ | (ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

የአሜሪካው ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ፣ ኢትዮጵያ በመጪው ሀምሌ ወር በህዳሴው ግድብ ላይ የተያያዘችው የውሃ ሙሌትን በተመለከተ አስተያየት ሰጥቷል።

በአስተዳደሩ ውስጥ ከውጪ ጉዳይ ከአገር ውስጥ ጉዳይ ጋር ጥምረት ያለው ፣በፕ/ቱ ታጭቶ ፣በምክር ቤቱ የሚጸድቀው ፣ ተጠሪነቱ ለፕሬዝዳንት ዶናል ትራምፕ የሆነው፣ የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት( National Security Council/NSC ) ዛሬ በትዊተር ገጹ ላይ ባወጣው አጭር መልእክት ” በምስራቅ አፍሪካ የሚገኙ ሁለት መቶ ሀምሳ ሰባት ሚሊዮን ሰዎች (ኢትዮጵይል፣ግብጽ እና ሱዳን) በህዳሴው ግድብ ዙሪይ በሚደርስ ፍትሃዊ የሆነ ስምምነት ፣ ከኢትዮጵያ በኩል ከሚሰነዘር ጠንካራ አመራር ላይ ጥገኛ ናቸው። ወቅቱ የህዳሴው ግድብን በውሃ ከመሙላት በፊት ከስምምነት ላይ መድረስን ይጠይቃል”ይላል።

ይህ በሮበርት ኦብሪያን የሚመራው የአሜሪካው የብሔራዊ ደህንነት ካውንስል የትዊተር መልእክት አንደምታን በተመለከተ አንድ ለኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ቅርበት ያለው ምንጭ ለህብር ራዲዮ ዝግጅት ክፍል በሰጠው አስተያየት “የግብጽ መንግስት በቅርቡ በፕ/ት አብዱል ፈታህ አልሲሲ እና በፕ/ት ዶናል ትራምፕ መካከል በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ውይይት ማድረጉን ይፋ አደረገ ፣ከትላንትና ወዲያ ደግሞ የህዳሴው ግድብ ድርድር በተፈለገው ፍጥነት እንዳልሄደ ግብጽ ኢትዮጵያን በመውቀስ ይፋ አደረገች፣ ዛሬ ደግሞ ለፕ/ት ትራምፕ ምክር እና መረጃ የሚያቀርበው የብሔራዊው ምክር ቤት ኢትዮጵያን የሚያስጠነቅቅ የሚመስል መግለጫ አወጣ፣ቀጣዩ አካሄድ ምን እንደሚሆን መገመት ቢከብድም ፣ የነገሮች ተዛማጅነትን መጠርጠር አይከብድም” ብለዋል።

በህዳሴውን ግድብ ድርድር ላይ ከአለም ባንክ ተወካይ ጋር በታዛቢነት ተጋብዞ የነበረው ፣ በሁዋላ ግን በገዛ ራሱ ወደ አደራዳሪነት እርከን የተሸጋገረው የአሜሪካ የገንዘብ ግምጃ ቤት ሹም የሆኑት ስቲቨን ሙኒችን ኢትዮጵያ ባለፈው የካቲት 28 ,2020 እኤአ ባልተካፈለችበት የዋሽንግተን ዲሲ ስብሰባ ላይ ” ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ሂደትን ስምምነት ሳይደርስ በምንም መልኩ እንዳት ጀምር”የሚል ፓለቲካዊ ትእዛዝ እና ጫና አዘል መግለጫቸውን እና በጊዜው የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ሚ/ር ጠንከር ያለ ምላሽን ያወሳው ምንጩ “የፕ/ት ትራምፕ አስተዳድር ግብጽን ለማስደሰት ሲባል የመሰለውን ውሳኔ ከመወሰን ስለማይመለስ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በሁሉም አቅጣጫ ተጠናክረው ሊዘጋጁ ይገባል” በማለት ታማኝ ምንጩ አክሎ ገልጿል ።

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top