Connect with us

የኦፌኮ ክስ

የኦፌኮ ክስ

ፓለቲካ

የኦፌኮ ክስ

የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከተደነገገ ወዲህ ዘጠና አንድ የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) አባላት፣ ደጋፊዎች እና የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ ዜጎች ተገድለዋል ሲል ፓርቲው ከሰሰ።

የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ በዛሬው ዕለት ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በፃፈው ደብዳቤ ከ100 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን ገልጿል። በዚህ ደብዳቤ ኦፌኮ በምዕራብ አርሲ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ቄለም ወለጋ፣ምሥራቅ ወለጋ፣ ምዕራብ ሐረርጌ፣ምዕራብ ጉጂ፣ ጅማ፣ ቦረና፣ ቡኖ በደሌ እና ሰሜን ሸዋ ዞኖች የተገደሉ እና የታሰሩ ሰዎችን ስም ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

ኦፌኮ እንደሚለው በምዕራብ ወለጋ ዞን ላሎ አሳቢ በተባለ ወረዳ ብቻ ሶስት ወንድማማቾች በጸጥታ ኃይሎች «ከእስር ቤት ተወስደው በአሰቃቂ ሁኔታ» ተገድለዋል። በዚያው በምዕራብ ወለጋ በነጆ እና ቦጂ ጮቆርሳ ወረዳዎች ወንድማማቾች በጸጥታ ኃይሎች ተገድለዋል ሲል የኦፌኮ ደብዳቤ ይወነጅላል።

የፓርቲው አመራሮች፣ አስተባባሪዎች እና ደጋፊዎችን ጨምሮ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ዞኖች ከ100 በላይ ሰዎች እንደታሰሩ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አስታውቋል።

የፓርቲው ሊቀ-መንበር ኘሮፌሰር መረራ ጉዲና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በጻፉት ደብዳቤ መንግሥት ከዚህ ቀደም የሚከሰስበት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች አባላትን «አሳድዶ የማሰር፣ ከፍ ሲልም የመግደል» ድርጊት እየተባባሰ ሔዷል ሲሉ ከሰዋል።

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀ-መንበር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጉዳዩን እንዲመረምሩ ጠይቀዋል። «የታሰሩ ዜጎች እንዲፈቱ፤ የተጎዱ ዜጎች ሕክምና እና ካሳ እንዲያገኙ፤ ከሕግ አግባብ ውጪ ዜጎችን ያሰሩ፣ ያሳሰሩ፣ ያንገላቱ፣ በማንአለብኝነት ሕይወት ያጠፉ እና ንብረት ያወደሙ ባለሥልጣናት ለሕግ ሊቀርቡ» ይገባል ብለዋል።(DW

Click to comment

More in ፓለቲካ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top