Connect with us

በጠቅላይ ሚ/ር አብይ የተስተጋባው “እርባና ቢስ አጋሰሶችን” ከኮቪድ-19 የመታደጉ ጩኸት

በጠቅላይ ሚ/ር አብይ የተስተጋባው “እርባና ቢስ አጋሰሶችን” ከኮቪድ-19 የመታደጉ ጩኸት

ጤና

በጠቅላይ ሚ/ር አብይ የተስተጋባው “እርባና ቢስ አጋሰሶችን” ከኮቪድ-19 የመታደጉ ጩኸት

በጠቅላይ ሚ/ር አብይ የተስተጋባው “እርባና ቢስ አጋሰሶችን” ከኮቪድ-19 የመታደጉ ጩኸት
በአምኃየስ ታደሰ
amhayest@gmail.com

በቁጥር 214 በአመዛኙ ስልጣን ከለቀቁ በኋላ ድምፃቸው ተሰምቶ የማይታወቅ አሜሪካውያንን የማይጨምር መራኄ-መንግስታት እንዲሁም የተወሰኑ የዓለም አቀፍ የተራድኦ እና የፋይናንስ ተቋማት ተጠሪዎች መጋቢት 26 ቀን 2012 ዓ. ም. ለ20ዎቹ ባለ-ፀጋ አገራት መንግስታት ያቀረቡትን ጥሪ ተከትሎ “ለአፍሪካ የ150 ቢሊዮን ዶላር አስቸኳይ የኮቪድ-19 ድጋፍ እንዲደረግ” የጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በያዝነው ሳምንት ደግሞ “በታላቁ ጅማሮ” (Great Reset) ዙርያ በተደረገው የዓለም የምጣኔ ኃብት መድረክ (World Economic Forum) ላይ ከዚሁ መታደማቸው ተዘግቧል፡፡

በዚሁ ድሆችን ታደጓቸው የሚል እንደምታ ባለው ደብዳቤ ላይ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ማመስገናቸው የዓለም አቀፍ ተሰሚነታቸው መገለጫ ሆኖ ሊያኮራ የሚችለው አጀንዳው በርግጥም የጤና ከሆነ እና ከሕዳሴ ግድብ ጋር ተያይዞ የተገለጸው የእርሳቸው በብሄራዊ ጥቅም ዙርያ ያለመደራደር አቋም አፍሪካውያንን በመታደግም ከተጠበቀ ይመስለኛል፡፡

የእርዳታ ጥሪውን መደገፋቸው የተጠቀሰው የኋላ ቀር አገራት መሪዎች ፍላጐታቸውን በቀጥታ ከመግለጽ ይልቅ አማላጅ ለምን እንዳስፈለጋቸው ደብዳቤው ባይገለጽም ሃብታሞቹ እንዲሰጡ የተፈለገው ምላሽ ከጤና እና ምጣኔ ኃብታዊ እርምጃዎች ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ሽማግሌዎቹ ከቶውኑ እስከዛሬ ድረስ በምድራችን መገኘቱ ላልተረጋገጠው የኮቪድ-19 ክትባት ከፍተኛውን ድርሻ የያዘው 3 ቢሊዮን ዶላር በጀት በአስቸኳይ እንዲመደብ ለመጠየቅ ያነሳሳቸው በመጃጀታቸው ምክንያት ነው የማያስብለው አያይዘው ከሞላ ጐደል የቢል እና ሜሊንዳ ፋውንዴሽን ኩባንያዎች ጥምረት የሆነው ጋቪ ክትባቱን በፍትሃዊነት እንዲያሰራጭ በተጨማሪ የሚያስፈልገው የ7.4 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ሙሉ በሙሉ እንዲተካለት ከማሳሰባቸው አንፃር ጭምር ነው፡፡

ነገረ ፈጆቹ ተጨማሪ 2.25 ቢሊዮን ዶላር በያዝነው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ላይ ይኖራሉ ላሏቸው 100 ሚሊዮን የኮቪድ 19 ሕሙማን የፀረ-ቫይረስ ሕክምና አቅርቦት እንዲውል ይማፀኑ እንጂ በበሽታው ሕይወታቸው ሊያልፍ የሚችለው በድምሩ ከ900,000 የማይበልጡ ኤስያውያን እና ከ300,000 ያነሱ አፍሪካውያን ሊሆኑ እንደሚችሉ የተጭበረበረው የለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ መተንበዩን በተመሳሳይ ደብዳቤ ላይ ከመግለጽ አልተቆጠቡም፡፡ እንዲያም ሆኖ እነሱ ከጠቀሱት ከእጥፍ በላይ አሃዝ ያላቸው አፍሪካውያን በሳንባ ነቀርሳ እና በወባ በየዓመቱ መሞታቸው ይልቁንም ከዓለማችን የኮቪድ-19 ተጠቂዎች የአፍሪካውያን ድርሻ 3 በመቶ ያነሰ የመሆኑ እውነታ ትዝ ያላቸው አይመስልም፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት በያዝነው ዓመት ባስቸኳይ ያስፈልገዋል ካሉት 1 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ 35 ቢሊዮን ዶላር በሂደት ሊቀርብለት እንደሚገባ የመሞገት ድፍረት ያገኙት እኚሁ ግለሰቦች በያዝነው ሳምንት ግብረ-ሰዶማውያንን እንኳን አደረሳችሁ ሲሉ የተደመጡት ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከተሾሙ አንስቶ ተቋማቸው የገንዘብ አጠቃቀሙን ያስመለከተ ሪፖርት አለማቅረቡን ብቻ ሳይሆን ድርጅቱ የኮቪድ-19 በሽታን ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ብሎ ያወጀው ከቢል ጌትስ ለተበረከተለት የ50 ሚሊዮን ዶላር ድጐማ ምላሽ ብቻ ሲል እንደሆነ ፎክስ ኒውስ ባለፈው ሳምንት መዘገቡን ሳይሰሙ በመቅረታቸው ሊሆን አይችልም፡፡

ሌላው በወረርሽኙ የተነሳ ድጋፍ የተጠየቀላቸው አገራት የገጠማቸውን ቀውስ ለመታደግ ዶ/ር አብይ ያስተጋቡትን የ150 ቢሊዮን ዶላር ምጣኔ ኃብታዊ እርዳታ አንገብጋቢነት ከመጠቆም ያልተገቱት እኚሁ ተቆርቋሪዎች የዓለም ባንክ እና ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) ከ500 ቢሊዮን እስከ 600 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ተጨማሪ ገንዘብ በብድር መልክ ለማቅረብ ዝግጁነት እንዳላቸው በማስረገጥ በተለይ የውጪ ምንዛሪ አቅርቦትን ከማመቻቸት (swap) አንፃር ኋላ ቀር አገራቱ የፋይናንስ ስርአታቸውን ለድንበር ዘለሎቹ የፋይናንስ ተቋማት አሳልፈው እንዲሰጡ እንደሚጠበቅ ምክረ ኃሳባቸውን ሰንዝረዋል፡፡

በርግጥም በኮቪድ-19 ምክንያት ወረርሽኝ ተከስቶ ጥፋቱ የምፅአት ቀን ገፅታ እንዳለው ከታመነበት በቀረበው የምልጃ ላይ የሚነሳ ጥያቄ የመፀወተን እጅ እንደ መንከስ ካስቆጠረ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሊቀርብ ይገባል የተባለውን እርዳታ ዓይነተኛ ተጠቃሚ ጨምሮ እንደ ጆርጅ ሶሮስን የመሳሰሉትን የደብዳቤው ፈራሚዎች ማንነት እና ፍላጐት ማንነት ካለማወቅ ሊሆን ይችላል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ በተመሳሳይ ደብዳቤያቸው ላይ እጃቸውን እንኳ መታጠብ እንደማይችሉ የገለጿቸው የትናንት ቅኝ ተገዥዎቻቸው የነበሩት አፍሪካውያን ዛሬም የሰቆቃ ሕይወት ለመግፋት የተገደዱት በእኚሁ የአዞ እንባቸውን የሚያፈሱ የቀድሞ መሪዎች የተሳሳተ የፖሊሲ አቅጣጫ ጭምር መሆኑን ተገንዝበው ሊጸጸቱ ይችሉ ይሆናል ተብሎ ስለማይታሰብ በመሆኑ አይደለም፡፡

ሰው ሰራሽ ነው ለሚሉት የከባቢያዊ አየር ለውጥ መፍትሄው የሕዝብ ቁጥር መቀነስ መሆኑን እንዲሁም ምፅዋት የሚጠይቁላቸው የኋላ ቀር አገራት ዜጐች እርባና ቢስ አጋሰሶች (useless eaters) ስለመሆናቸው ከሚያምኑት አንስቶ የኢትዮጵያ ዓመታዊ የጤና በጀት የምድራችን ተቀዳሚ ባለ-ፀጋ ከሆነው የአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ 1 በመቶ ጥሪት ያነሰ እንደሆነ ሲነግሩን የምናስታውሳቸው ሕልውናቸውን በድህነታችን ላይ ያደረጉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጭምር ለችግራችን መፍትሄው ፍትሃዊ የሃብት ክፍፍል ነው ብለው እንዲያስቡ አይጠበቅም፡፡

መሠረታዊ ፍላጐታችንን ማሟላት ወይም በሽታን ለመከላከል የሚያስፈልገን የተመጣጠነ ምግብ እና የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ሳይሆን ልንመጸወት የሚገባው የፋርማሲ መድሃኒቶች እና ክትባቶች .ጐን ለጐንም ተበድረንም የምናገኘውን ገንዘብም የሠራተኞችን ጅምላ ቅነሳ ለመታደግ ለሚያስችል እና የፍጆታ ወጪን ለመሸፈን እንድናውለው እንጂ የመሠረተ ልማት አውታሮች ግንባታን እንድናካሂድበት የሚመክሩን ካልሆነ በርግጥም የውጥኑ ተጠቃሚዎች እኛ እንጂ ሌሎች አለመሆናቸውን ማረጋገጥ የእኛ በተለይም የመሪዎቻችን ተቀዳሚ ተግባር መሆኑ አይታበልም፡፡

የኡኡታው እንደምታ ከምናውቀው በተቃራኒ በተለይም ለክትባቶች ዝግጅት መሠረት የሆኑት ቫይረሶች ወይም ሌሎች ተሕዋሲያን የሚያስከትሉት ጉዳት ሊከላከሉ ከሚታሰበው በሽታ የገዘፈ መሆኑን ማስረገጥ የተለየ ምርምር አለመጠየቁ ነው፡፡ በተጨማሪም የመጀመሪያውን የዓለም ጦርነት ተከትሎ የተከሰተው እና 5ዐ ሚሊዮን ሕዝብ እንደጨረሰ የምናውቀው በተለምዶ የስፓኒሽ ፍሉ እየተባለ የሚጠራው በሽታ መንስኤው ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፍ ጀርም መሆኑ ካለመረጋገጡም በላይ በወረርሽኙ ሙሉ በሙሉ ሕይወታቸው ያለፈው ለተለያዩ በሽታዎች አስቀድሞ ክትባት የተሰጣቸው እንደነበሩ መቀበል ቢያዳግትም አለመነገሩ ሃቅ ከመሆን አያግደውም፡፡

ዛሬ ከአምስት አሜሪካውያን አንዱ የመማር ስንኩል (learning disabled) ሲሆን ከ31 የአገሪቱ ሕፃናት አንዱ ደግሞ የአዕምሮ ዝግመት ወይም የኦቲዝም ተጠቂ ሊሆኑ የቻሉት በጨቅላዎቹ የ9 ወር እድሜ ግድም የሚሰጡት የኤምኤምአርን የመሳሰሉ ክትባቶች በውስጣቸው በያዟቸው ደም ወደ አንጐል እንደፈለገ እንዳይዘልቅ የሚገድቡትን (blood brain barriers) ሕዋሳት ተግባራት ለማወክ የዋሉ የአሉምኒየም ስሪት የሆኑ የናኖ ክፋዮች መሆናቸው በእንስሳት ሞዴሎች ላይ በተካሄዱ ምርምሮች ቢረጋገጥም እውነታው ተዳፍኖ የቀረው ጤንነታችን የተቆጣጠሩት እና በበሽታ መነገድን የተካኑት ወገኖች የመረጃ ምንጮቻችንም ባለቤቶች በመሆናቸው የተነሳ ብቻ ነው፡፡

ለዲጂታል ክትባት የሚደረገው ሩጫ ያልተዋጠላቸው የሩስያው ኘሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከእንግሊዝ ጋር በሂደቱ ዙርያ የመተባበር ፍላጐት እንደሌላቸው ይፋ ሲያደርጉ ወይም ኘሬዝዳንት ዶናልድ ትራምኘ ደግሞ ኮቪድ-19 በሰፊው የሚወራለት ክትባት ከመገኘቱ በፊት ከምድራችን እንደሚጠፋ ያላቸውን እምነት መግለፃቸው ሲታሰብ የእኛዋ ኘሬዝዳንት ሳሕለወርቅ ዘውዴ ደግሞ በትዊተር ገፃቸው አማካይነት ጭምር ያቀነኑለት ክትባት ቢገኝ እንኳን ውጤቱ እንደጠበቁት መሆኑን እጠራጠራለሁ፡፡

ምክንያቱም የአርኤንኤ የሚባሉት ኮሮናን መሰል ቫይረሶችም ሆኑ ኤችአይቪ የሚመደብባቸው ሪትሮቫይሶች መደበኛው ሥነ ቫይረስ በተለይም የኮች ፖስቹሌት በሚጠይቀው መንገድ የበሽታ መንስኤ መሆን መቻላቸው ካለመረጋገጡም በላይ በእኚሁ የቫይረሶች ንዑስ ስብስቦች ዙርያ ላለፉት 4ዐ ዓመታት ተደርጐ በሰብአዊ ፍጡራን ላይ ውጤታማ የሆነ አንድም ተስፋ ሰጪ ክትባት ሊገኝ ቀርቶ ሙከራ የተደረገባቸው እንስሳትም ለከፋ የጤና ችግር እና ሞት መዳረጋቸውን ለመገንዘብ የሚጠይቀው ጥረት መሪ ከመሆን ብቃት ጋር ፈጽሞ ስለማይመጣጠን ነው፡፡

በመጨረሻም ፈጣሪ ለኮቪድ-19 የሚደረገው ምርመራ ምንነት ተገንዝበው አገራቸው ሙሉ በሙሉ ከበሽታው ነፃ መሆንዋን ከጥቂት ቀናት በፊት እንዳሳወቁት የታንዛንያው ኘሬዝዳንት ማጉፉሊ እውነታውን ለሁላችንም በተለይም ለመሪዎቻችን እንዲገልጽልን በመመኘት የምቋጨው ጽሁፌ ካስከፋም ናታን ፍሬዘር በሁለት ከሚከፍላቸው ሰዎች መካከል መንግስት እንደሚያስቡት የሚያምኑትን እንጂ ራሳቸው የሚያስቡትን እንደማይሆን ካለኝ ተስፋ ጭምር ነው፡፡

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top