Connect with us

ታዋቂው የሲቪል መብት ተሟጋች ኮንግረሱ ኢትዮጵያን የሚደግፍ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠየቁ

ታዋቂው የሲቪል መብት ተሟጋች ኮንግረሱ ኢትዮጵያን የሚደግፍ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠየቁ
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

ታዋቂው የሲቪል መብት ተሟጋች ኮንግረሱ ኢትዮጵያን የሚደግፍ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠየቁ

ታዋቂው የሲቪል መብት ተሟጋች ኮንግረሱ ኢትዮጵያን  የሚደግፍ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ጠየቁ

የህዳሴ ግድብን እና ግብጽን በተመለከተ የአሜሪካ ኮንግረስ ኢትዮጵያን የሚደግፍ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያሳልፍ ታዋቂው የሲቪል መብት ተሟጋቹ ጀሴ ጃክሰን ጠየቁ።

ጀሴ ጃክሰን በኮንግረሱ ለጥቁር ኮከስ ቡድን መሪ ግብፅ ሰሞኑን ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የዓባይ ወንዝን በተመለከተ ስላስገባቸው ሰነድ ደብዳቤ ጽፈዋል።

በደብዳቤያቸውም ኮንግረሱ ናይል እና ግብጽን በተመለከተ ኢትዮጵያን የሚደግፍ የውሳኔ ሃሳብ እንዲያሳልፍ ጠይቀዋል።
ግብጽ በናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ከዚህ በፊት ያለ ኢትዮጵያ ይሁንታ የተደረሱ የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን ለመተግበር ትሞክራለችም ብለዋል።

ለአብነትም በፈረንጆቹ 1929 እና 1959 የተደረሱ የቅኝ ግዛት ስምምነቶችን ጠቅሰው፣ ስምምነቶቹ ግብጽ እና ሱዳን ያለ ኢትዮጵያና ያለ ሌሎች የናይል ተፋሰስ አገራት ይሁንታ የተፈረሙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም ግብጽ እና ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ የአንበሳውን ድርሻ በብቸኝነት እንዲይዙ የሚያደርግና ዓለም አቀፍ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን በተመለከተ የተደረሱ መርሆዎችን የጣሰ መሆኑንም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ግብጽ ኢትዮጵያን ሳታማክርና ሳታወያይ ናይል ወንዝን ተጠቅማ የአስዋን ግድብ መገንባቷንም ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ ከናይል ወንዝ 85 በመቶውን ድርሻ ታዋጣለች ያሉት ጀሴ፣ ይሁን እንጅ የተፈጥሮ ጸጋዋ የሆነውን የአባይ ወንዝን እንዳትጠቀም ግብጽ የምትከተለው አካሄድ ከህግም ሆነ ከሞራል አኳያ ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።

በተጨማሪም የአሜሪካ መንግሥትና የዓለም ባንክ በግብጽ ላይ የኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ ፀጋዋን የመጠቀም መብቷን ታሳቢ ያደረገ ውሳኔ እንዲያሳልፉም ጠይቀዋል::

ካይሮም አሁን ላይ አሜሪካ እና የዓለም ባንክን በመጠቀም በሌሎች የተፋሰሱ አገራት ላይ የቅኝ ግዛት ውል ለመጫን እየሞከረች መሆኑንም በደብዳቤያቸው አመልክተዋል ።

ከዚህ አንጻርም የአሜሪካ መንግሥትም ሆነ የዓለም ባንክ የአደራዳሪነት ሚና እንደሌላቸው በማንሳትም አሜሪካም ከቅኝ ግዛት ውል እቅድ ልትወጣ ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

አዲስ ዘመን ግንቦት 14/2012

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top