Connect with us

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአፍና የአፍንጫ መከለያ አላደረጉም በሚል …

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአፍና የአፍንጫ መከለያ አላደረጉም በሚል እየተፈጸመ ያለውን እስር አወገዘ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአፍና የአፍንጫ መከለያ አላደረጉም በሚል …

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የአፍና የአፍንጫ መከለያ አላደረጉም በሚል እየተፈጸመ ያለውን እስር አወገዘ

የኮሚሽኑ ኮሚሽን ዶክተር ዳንኤል በቀለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአፍና የአፍንጫ መከለያ አለደረጉም በማለት በጎዳና ላይ ሰዎችን እያሰረ ያለው ከህግ ውጭና የዘፈቀደ እርምጃ ነው በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ብለዋል።

በአዋጁ መስረት የተጣለው ግዴታ የሚለው ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥበት ስፍራዎች እና ብዙ ህዝብ የሚገኝባቸው አካባቢዎች ላይ ግዴታ የጣለ ቢሆንም ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እየወሰደ ያለው እርምጃ የዘፈቀደ እርምጃ ነው እጅግ በአስቸኳይ ሊቆም እንደሚገባ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።

እርምጃው ተገቢ አይደለም ማለት ግን የአፍና የአፍንጫ መከለያ አየስፈልግም ማለት አይደለም ፣ ማህበራዊ ርቀት መጠበቅ በማይቻልበት አከባቢ የፊት መሸፈኛ መጠበቅ መበረታታት አለበት እኛም ይህንን መልዕክት እናስተላልፍለን ብለዋልም ኮምሽነሩ፡፡

ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥበት ስፍራዎች እና ብዙ ህዝብ ከሚበዛባቸው አካባቢዎች ውጪ በጎዳናዎች ላይ አፍና የአፍንጫ መከለያ አላደረጋችሁም በማለት ሰዎችን ማሰር እና በአንድ ቦታ ማሰር ተመጣጣኝ ያልሆነ እርምጃ መሆኑን ዶክተር ዳንኤል ተናግረዋል ፡፡

አሁን እየደረሰን ባለው መረጃ መሰረት ፣ በትምህርት ቤት ውስጥ የታሰሩ ሰዎች አሉ ይህ ደግሞ የበለጠ ለአደጋ ያጋልጣል እርምጃውም ተመጣጣኝ አይደለም ብለዋል፡፡

ህዝባዊ አገልግሎት በሚሰጥበት ስፍራዎች እና ብዙ ህዝብ ከሚበዛባቸው አካባቢዎች አዋጁ እርምጃ ለመውሰድ ስለሚፈቅድ መተግበር አለበት አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃ አንደኛ ከአዋጁ ውጪ ነው ፣ ሁለተኛ ከነገሩ ሁኔታ ጋር ተመጣጣኝ እርምጃ አይደለም ፣ ሶስተኛ ለበለጠ አደጋ ያጋልጣል ጠቃሚ እርምጃ አይደለም በአስቸኳይ ይቁም ብለዋል ኮምሽነሩ፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በዳንኤል መላኩ
ግንቦት 5 ቀን 2012 ዓ.ም

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top