Connect with us

ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው በተገኙ 268 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው በተገኙ 268 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው በተገኙ 268 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

ፖሊስ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈው በተገኙ 268 አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ ወሰደ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ክልከላውን ተላልፈው በተገኙ 268 አሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ ይፋ እንዳደረገው የትራፊክ ቁጥጥር መምሪያ ካለፈው መጋቢት 28 እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2012 ዓ.ም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፅም ቁጥጥር አድርጓል።

በዚህም 195 አሽከርካሪዎች ከተፈቀደው በላይ ተጨማሪ ሰው በመጫንና 73 አሽከርካሪዎች ደግሞ ከተፈቀደው ታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ መያዛቸውን የትራፊክ ክፍሉ የህዝብ ግንዛቤ ማሳደጊያ ድቪዚዮን ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ሠለሞን አዳነ ገልፀዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ ስርጭትን በመቆጣጠርና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ በወጣው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጭዎች ካላቸው የወንበር ቁጥር በግማሽ መቀነስ አገልግሎት መስጠት እንዳለባቸው ተደንግጓል።

በዚህ አገልግሎት ተሳፋሪዎች መክፈል ያለባቸው ሂሳብ ተወስኖ እያለ ተጨማሪ ሲያስከፍሉ የነበሩ አሽከርካሪዎች ተገኝተዋል።

በመሆኑም የተቀመጠውን አሰራር ተላልፈው የተገኙ 268 አሽከርካሪዎች ህጋዊ እርምጃ ተወስዶባቸዋል።

በተመሣሣይ ተሣፋሪውን ማስከፈል ከሚጠበቅባቸው ታሪፍ በላይ ሲያስከፍሉ የተገኙ አሽከርካሪዎች መኖራቸውን ኃላፊው ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ ደንብ ላይ እንደተቀመጠው ከ50 ፐርሰንት በላይ መጫን በየደረጃው የ5 ሺህ ብር ቅጣትና መንጃ ፍቃድም ጭምር እስከመነጠቅ የሚያደርስ እርምጃ ያስወስዳል።

ኢዜአ ሚያዚያ 12/2012

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top