Connect with us

ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
Photo Facebook

ህግና ስርዓት

ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 12 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስለ ዋሉ።

ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በቦሌ አየር መንገድ፣ ጋላፊ፣ ሞያሌ፣ አዋሽ፣ ጅጅጋ፣ መቀሌ፣ ጅማ፣ ቡታ ጅራ፣ ሁመራ፣ ቶጎውጫሌ እና ሞጆ ኬላ መቆጣጠሪ ጣብያዎች ሲሆን የተለያዩ ዓይነት አልባሳት፣ ጥራቱ ያልተረጋገጠ የምግብ ዘይት፣ ቡና፣ ሱካር፣ ኤሌክትሪኒክስ፣ ምግብና ምግብ ነክ ዕቃዎች እንዲሁም የተለያዩ ዓይነት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በሀሰተኛ ሰንድ ጭምር በህገ-ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጓል፡፡

እንደሚታወቀው በአሁኑ ጊዜ ሀገራችን ብሎም በአለም የኮሮናቫይረሰ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመቆጣጠር ደፋ ቀና ባለችበት ሰዓት፣ ቫይረሱ የብዙ ሰዎችን ሕይወት እየቀጠፈና በከፍተኛ ፍጥነ እየተሰፋፋበት እና በኢኮኖሚው ላይ ብዙ ጫና እየፈጠረ ባለበት በዚህ ወቅት ስለ ሀገር እድገት ግድ የማይላቸው በጣም ጥቅት ግለሰቦች አልተሳካላቸውም እንጂ በሕገ-ወጥ ንግድ ላይ በመሰማራት ላይ ተጠምደዋል፡፡

የሚቀድመው ግን ህዝብን እና ሀገርን ከወረርሽኙ መከላከል ነበር፡፡ ደሃውን ማህበረሰብ መደገፍ ነበር፡፡ ይህንን በጎ ሥራ መስራት እየተቻለ ሀገርቷ ማግኘት ያለባትን ገቢ በማጨበርበር ፣ በህገ-ወጥ ንግድና የኮንትሮባንድ ዕቃዎችን በማስገባትና በማስወጣት በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡

ሆኖም ግን ኮንትሮባንድና ህገወጥ ተግባር ለመከላከል የተሰማሩ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞችና አመራሮች እንዲሁም አጋር አካላት በዝናብ፣ በፀሐይና በኮንትሮባድስቶች ዛቻ ሳይበገሩ ለሚወዱት ሀገራቸውና ህዝባቸው ብዙ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴርም ይህን ህገወጥ ተግባር ለመከላከል የተሳተፉት ኮሚሽኑ ሠራተኛችና አመራሮች እንዲሁም ለአጋር አካላት ከፍተኛ ምስጋና እያቀረበ ከወረርሽኙ እራሳቸውን እየጠበቁ በስራቸው እንዲጠናክሩ አገራዊ ጥሪውን ያቀረበል፡፡

(የገቢዎች ሚ/ር)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top