Connect with us

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች
Photo BBC

ጤና

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች

የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ማንኛውም ግለሰብ የሚከተሉትን ቅድመ ጥንቃቄዎች ሊያደርግ እንደሚገባ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት  አሳስቧል።

ለእጅ ንጽህና መጠበቂያ የሚሰሩ አልኮል ነክ ምርቶችን መጠቀም

ባልታጠበ እጅ አይን፣ አፍንጫ እና አፍን አለመንካት

ቫይረሱ ሪፖርት ከተደረገባቸው ሀገራት የመጡ ተጓዦች ሆነው የበሽታውን ምልክት ከሚያሰዩ ሰዎች ጋር ንክኪ አለማድረግ

በተጫማሪም ከ1 እስከ 2 ሜትር ርቀት መጠበቅ

ስለቫይረሱ በቂ መረጃ በማግኘት መተግበር ፣

በቫይረሱ መያዛቸውን የተጠረጠሩ ሰዎች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች፦

ወደ ሀገር በተመለሱ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ የመተንፈሻ አካል ህመም፣ ትኩሳትና እንደሳል ያሉ የህመም ምልክቶች ካለብዎት ወዲያውኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት ማግኘት፣
የቫይረሱ ስሜት ከመፈጠሩ አስራ አራት ቀናት በፊት ቫይረሱን ሪፖርት ወዳደረጉ ሃገራት ሄደው ከነበረ ይህንንም ለጤና ባለሙያው ማስረዳት፤

በሚያስሉበትና በሚያስነጥሱበት ጊዜ ቫይረሱ ወደ ጤነኛሰው እንዳይተላለፍ አፍና አፍንጫን በክንድ፣ በመሃረብ ወይም በሶፍት መሸፈን፣

አፍና አፍንጫን ለመሸፈን የተጠቀምንበትን ሶፍት በአግባቡ በቆሻሻ መጣያ ውስጥ ማስወገድ እና እጅን ሁልጊዜ በውሃና በሳሙና መታጠብ ያስፈልጋል።

ቫይረሱን ሪፖርት ወዳዳረጉ ሀገራት ሄዶ የቫይረሱን ምልከቶች ማሳየት የጀመረ ሰውን የሚያውቅ ማንኛውም ሰው በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቋም ማሳወቅ ወይም ከታች በተገለፁት አድራሻዎች በመጠቀም ሪፖርት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top