Connect with us

ልማት ባንክ የማይመለስ የብድር መጠኑ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ልማት ባንክ የማይመለስ የብድር መጠኑ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ህግና ስርዓት

ልማት ባንክ የማይመለስ የብድር መጠኑ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ

ልማት ባንክ የማይመለስ የብድር መጠኑ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ደረሰ
~ ከተበዳሪዎቹ 71 ያህሉ ጠፍተውበታል፣

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በመንግስት ኃላፊዎች ጣልቃ ገብነት፤ በባንኩ ሠራተኞችና ኃላፊዎች በጥቅም መደለል ምክንያት ከሰጠው ብድር ውስጥ ከ16 ቢሊዮን ብር በላይ ሊመለስ የማይችል (የተበላሸ) መሆኑን አስታወቀ።

ባንኩ 86 ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ብር ዕዳ ያለበት መሆኑን፣ 39 ቅርንጫፎቹን መዝጋቱንና 71 ተበዳሪዎቹ እንደጠፉበትም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ሀይለየሱስ በቀለ፤ በትላንትናው ዕለት የባንኩን የስድስት ወር የስራ አፈጻጸምና የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ ዕቅድ አስመልክቶ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ ባንኩ ለ16 ነጥብ አራት ቢሊዮን ብር የብድር ብልሽት የተዳረገው የመንግስት ሥራ አስፈፃሚዎች ጣልቃ ገብነት፣ የባንኩ ሠራተኞችና ኃላፊዎች በጥቅም በመደለል በብድር መስጠታቸው ነው፡፡ እንዲሁም የፕሮጀክቶቹን የአዋጭነት ጥናት ሳይደረግና የተበዳሪዎቹ አቅም ሳይታወቅ ብድር እንዲሰጣቸው በመደረጉ ነው ብለዋል።(ኢ.ኘ.ድ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top