Connect with us

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ በሮም ከሚገኙ ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ በሮም ከሚገኙ ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ዜና

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ በሮም ከሚገኙ ዓለም ዓቀፍ ድርጅት ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጣሊያን ጉብኝታቸው ጎን ለጎን ተቀማጭነታቸው ሮም ከሆኑ ዓለም ዓቀፍ ድርጅቶች የሥራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።

ሚኒስትሩ ከዓለም የእርሻና ምግብ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ኩ ዶንገዩ፣ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ባስሌይ እና ከዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ ፕሬዚዳንት ጊልበርት ሁንግቦ ጋር ነው የተወያዩት።

በውይይታቸውም ድርጅቶቹ በኢትዮጵያ የጀመሯቸውን የልማት ፕሮጀክቶች በሚጠናከሩበት ሁኔታ እና ከሀገሪቱ ጋር ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ትብብር አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረዋል።

አቶ ገዱ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ባስሌይ ጋር በነበራቸው ውይይት ድርጅቱ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ሰብዓዊ ድጋፍ አጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።

ከዓለም እርሻና ምግብ ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ኩ ዶንገዩ ጋርም ድርጅቱ በሀገሪቱ የተከሰተውን የበርሃ አንበጣ ለመከላከል ለሚሰሩ ስራዎች እና ለኢትዮጵያ ግብርና ትራንስፎርሜሽን የሚደረጉ ድጋፎች እና ትብብሮች በሚጠናከሩበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የእርሻ ልማት ፈንድ ፕሬዚዳንት ጊልበርት ሁንግቦ ጋር ተቋሙ ለግብርናው ዘርፍ የሚያደርገውን የፋይናንስ ድጋፍ አጠናክሮ በሚቀጥልበት ሁኔታ ላይ መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top