Connect with us

የብሮድካስት ባለሥልጣን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ለኦ ኤም ኤን ማስጠንቂያ ሰጠ

የብሮድካስት ባለሥልጣን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ለኦ ኤም ኤን ማስጠንቂያ ሰጠ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የብሮድካስት ባለሥልጣን በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጉዳይ ለኦ ኤም ኤን ማስጠንቂያ ሰጠ

ለሰራው ጥፉት ይቅርታ ይጠይቅም ተብሏል፣

እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በጀዋር መሐመድ ይመራ ለነበረው የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (ኦ ም ኤን) ማስጠንቀቂያው ተሰጠው። ማስጠንቀቂያው የተሰጠው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጴጥሮሳውያን የቤተክርስቲያን ክብር እና መብት አስጠባቂ ኅብረት ለባለሥልጣኑ ባቀረበው አቤቱታ መነሻነት ሲሆን ፣ ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 533/99 በአንቀፅ 7 ንዑስ አንቀፅ 10 በተሰጠው ተግባር እና ኃላፊነት መሠረት በቀረበው ቅሬታ ላይ ተገቢውን ማጣራት በማድረግ የሚዲያ ተቋሙን ምላሽ እና ማብራሪያ ተመልክቶ በመመሪያ ቁጥር 03/2000 መሠረት በማጣራት ቅዳሜ ጥር 29 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3:30 ሰዓት በኦሮምኛ ቋንቋ በጣቢያው በተሰራጨው የኦፌኮ (የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ) በገብረ ጉራቻ እና ፍቼ ከተሞች ባከናወነው የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስል ሕዝባዊ ጉባዔ ላይ አቶ ኃ/ሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ ያደረጉት ንግግር ይዘት ከብሮድካስት አዋጅ 533/1999 አንፃር ያላከበራቸው ድንጋጌዎች ከተራ ቁጥር 1-4 ያሉትን በመጥቀስ የተፈፀመውን የሕግ ጥሰት ጉዳዮች የአዋጁን አንቀፅ 28(1) እስከ 30 (4) በተደነገገው መሠረት በወንጀል ተጠያቂ ከማድረግ ባለፈ ፈቃድ እስከ ማስነጠቅ የሚያደርስ እርምጃ እንደሚያስወስድ ለጣቢያው በተፃፈው ደብዳቤ ተገልጿል፡፡

OMN TV ለባለሥልጣኑ በሰጠው መልስ ቅሬታ “አቅራቢው በአካል በማይመለከተው እና መብቱን በማይጋፋ ጉዳዮች ላይ ያቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም ” በማለት ምላሽ ቢሰጥም የብሮድካስት ባለሥልጣን በአዋጁ አንቀፅ 42 መሠረት የጣቢያውን ምላሽ ውድቅ በማድረግ OMN TV የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቅ ወስኖበታል፡፡

በተጨማሪም OMN TV ቅሬታ በቀረበባቸው ይዘቶች ዙሪያ የቤተክርስቲያኗን ቅሬታ በተመጣጣኝ ስፋት እና በተመሣሣይ የሥርጭት ሰዓት አስተናግዶ ሪፖርት እንዲያደርግ የታዘዘ ሲሆን ፣ ፊት በሕግ አግባብ ብቻ ሀገራዊ ሰላምን የሚያደፈርስ የሕዝቦች አብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽር መልዕክት እንዳያስተላልፍ እና ሙያዊ ሥነ ምግባርን አክብሮ እንዲሰራ በማለት በቀን 18/06/2012 ዓ.ም በተፃፈ 4 ገፅ ደብዳቤ የብሮድካስት ባለሥልጣን ለOMN TV ከባድ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡

(መ/ር አቤል አሰፋ © EOTC TV)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top