Connect with us

የእግረኞች በሞባይል ጽሑፍ እየተላላኩ መጓዝ የበለጠ ለትራፊክ አደጋ ያጋልጣል – ጥናት

የእግረኞች በሞባይል ጽሑፍ እየተላላኩ መጓዝ የበለጠ ለትራፊክ አደጋ ያጋልጣል - ጥናት
Photo: Facebook

ማህበራዊ

የእግረኞች በሞባይል ጽሑፍ እየተላላኩ መጓዝ የበለጠ ለትራፊክ አደጋ ያጋልጣል – ጥናት

በካናዳ የተጠና አንድ ጥናት አግረኞች በመንገድ ላይ የፅሁፍ መልዕክት እየተላላኩ መጓዝ ሙዚቃ ከማዳመጥ እና በስልክ ከመነጋገር የበለጠ በከፍተኛ ሁኔታ ለአደጋ እንደሚያጋልጣቸው አመለከተ።

ተመራማሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ እግረኛ ላይ ከሚከሰቱ አደጋዎች በስተጀርባ ያሉትን ምክንያቶች ካጠኑ በኋላ ችግሩ ከፍተኛ ነው ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የጥናቱ ውጤት የጽሑፍ መልእክት እየላኩ መንገድ ማቋረጥ ወደ ግራ እና ወደ ቀኝ መመልከት አለመቻል ጋር ተያይዞ ለሚመጣ አደጋ ምክንያት ነው ብሏል።

በሌላም በኩል በስልክ ማውራት መንገዱን ለመሻገር ከሚወስደው ጊዜ ትንሽ ጭማሪ የሚያሣይ ሲሆን፥ ሙዚቃ ማዳመጥ በእግረኞች ደህንነት ላይ ትልቅ ለውጥ አላማምጣቱም ነው በጥናቱ የተመላከተው።

የእግረኞች መዘናጋት በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ከተሞች ውስጥ እየጨመረ የሚሄድ ችግር መሆኑን ጠቅሰው፥ በዚህ ዘርፍ ተጨማሪ ጥናት እንደሚያስፈልግ በካናዳ ካልጋሪ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ የሆኑት አጥኚ ቡድኖቹ ገልጸዋል።

የዕለት ተዕለት ኑሮ የሚካተቱትን የስማርትፎን ፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ መተግብሪያዎች፣ ቪዲዮዎች እና ሙዚቃዎች ጨምሮ ትኩረትን የሚከፋፍሉ የእግር ጉዞ እና የተዘበራረቀ የጎዳና ላይ ማቋረጦች የወደፊቱ የመንገድ ደህንነት አሳሳቢ ጉዳዮች መሆናቸውንም ተመራማሪዎች ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ሲ.ኤን.ኤን

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top