Connect with us

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች ህጋዊ ለማድረግ የምዝገባ ሥራ ተጀመረ

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች ህጋዊ ለማድረግ የምዝገባ ሥራ ተጀመረ
Photo: Facebook

ማህበራዊ

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ዜጎች ህጋዊ ለማድረግ የምዝገባ ሥራ ተጀመረ

በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የሚኖሩ መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን ህጋዊ ለማድረግ የምዝገባ ሥራ መጀመሩን
በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት አስታወቀ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከየካቲት 5-7 ቀን 2012 ዓ.ም በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ጉብኝት በማድረግ በመካከለኛው ምሥራቅ አገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በመገናኘት ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

በጉብኝቱ በተለይ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚኖሩ ዜጎቻችን ያለባቸውን ችግሮች ለማቅረብ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተደረገ ውይይት ስምምነት ከተደረሰባቸው ጉዳዮች መካከል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ዜጎቻችንን ህጋዊ ለማድረግ ስምምነት ተደርሶ እየተሰራበት ይገኛል፡፡

በዚሁ መሠረት ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ የዜጎች የመረጃ የማሰባሰብ ሥራ በአቡዳቢ ኤምባሲ እና በዱባይ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት በይፋ ተጀምሯል፡፡

ይህም ዜጎች ማንነታቸውን የሚገልፅ ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ህጋዊ መሆን የሚችሉበትን የጉዞ ሰነድ (ፓሰፖርት) እንዲዘጋጅላቸው የማድረግ እና በራሳቸው ፍላጎት ወደ አገር መመለስ ለሚፈልጉ ዜጎቻችን ፓሰፖርት የሌላቸው ወደ አገር መግቢያ የአንድ ጊዜ የጉዞ ሰነድ ሊሴ ፓሴ ይሰራላቸዋል፡፡ ይህንንም መረጃ በማሰባሰብ ከአገሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ የሚሰራ መሆኑን ታውቋል፡፡

በዱባይና ሰሜን ኤምሬቶች የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችንን በተለያዩ ምክንያቶች በህገወጥ አሰሪዎችና ደላሎች አማካይነት ለህገ ወጥነት በመዳረጋቸው መብታቸውን እና ክብራቸወን ለማስጠበቅ አዳጋች ሆኖ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ 7 ግዛቶች የሚኖሩ ዜጎቻችን ህጋዊ ሆነው መብታቸውና ክብራቸው ተጠብቆ እንዲሰሩ መንግስት እየሰራ መሆኑን በዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ክብርት ወ/ሮ እየሩሳሌም አምደማርያም ገልፀዋል፡፡ ዜጎች የዱባይ ቆንስላ ጽ/ቤቱ እና አቡዳቢ የሚገኘው ኤምባሲ እ.ኤ.አ ከፌብርዋሪ 23 እስከ ማርች 22 ቀን 2020 ድረስ ማንነታቸውን የሚገልጽ (ፓሰፖርት፣ ፓሰፖርት ኮፒ ወ.ዘ.ተ) በመያዝ እንዲገለገሉ እና ተጨማሪ መረጃዎችን እንደሚገልፅ ከዱባይ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top