Connect with us

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳሰበ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳሰበ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳሰበ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የተፈፀመውን እገታ በተመለከተ መንግሥት ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳሰበ

በሀገሪቱ ባሉት ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ በነበሩ የአማራ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ የእገታ እና የአፈና ድርጊት እንደተፈፀመ የምሁራን መማክርት ጉባኤው ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች መገንዘቡን አስታውቋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የፌዴራሉም ሆነ የክልሉ መንግሥታት ምንም ዓይነት ግልጽ መረጃ ለሕዝብ አለማሳወቃቸው እንዳሳሰበውም ነው ጉባኤው የገለፀው።

በአማራ ተወላጆች ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሱ በደሎችን በተመለከተ የፌዴራል መንግሥትም ሆነ የተለያዩ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ተገቢውን ትኩረት ሲሰጡ እንደማይታይም የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ አስታውቋል።

በመሆኑም በየደረጃው የሚገኙ የመንግሥት አካላት የእገታ እና የአፈና ድርጊት የተፈፀመባቸውን የአማራ ተማሪዎች በተመለከተ አፋጣኝ መረጃ ለሕዝብ እንዲሰጡና በአጭር ጊዜ አጣርተው አስፈላጊውን መንግሥታዊ ኃላፊነት እንዲወጡ ማሳሰቡን የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል።(የአማራ መገናኛ ብዙሀን)

Continue Reading
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top