Connect with us

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ማሳሰቢያ!

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ማሳሰቢያ!
አብመድ

ነፃ ሃሳብ

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ማሳሰቢያ!

የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ ማሳሰቢያ!

ምርጫው ፍትሐዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ የሌላ ብሔር ተወላጆች ውክልና መረጋገጥ እንዳለበት የአማራ ምሁራን መማክርት ጉባዔ አሳሰበ፡፡

ምርጫ ዜጎች የአንድ ሀገር አካል መሆናቸው የሚረጋገጥበት አንዱ እና ዋነኛው ፖለቲካዊ ሂደት ነው፡፡ በሁሉን አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌ፣ በዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን እና በአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብት ቻርተር እንደተደነገገው በአንድ ሀገር ውስጥ በምርጫ በመራጭነትም ሆነ በተመራጭነት መሳተፍ መሰረታዊ የሰው ልጆች መብት እንደሆነ ያስቀመጣል ነው ያለው ምሁራን መማክርቱ፡፡

በመሆኑም ይላል የምሁራን መማክርት ጉባዔ በመግለጫው “ዜጎች በሚኖሩበት አካባቢ በማንነታቸው የተነሳ በተለይም በተመራጭነት እንዳይሳተፉ ማድረግ ወይም አለማመቻቸት መሰረታዊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው” ይላል፡፡ መሰል የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዳይፈፀሙም በየደረጃው ያሉ የመንግሥት ተቋማት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ግዴታ እና ኀላፊነት እንዳለባቸው ይጠቁማል፡፡

ኢትዮጵያ ከደርግ መውደቅ ማግስት የይስሙላ ምርጫ እንዳካሄደች የሚያወሳው የምሁራን መማክርት ጉባዔው መግለጫ ከአንኳር ጥፋቶች መካከል አንዱ “በብሔራቸው ከተሰየሙ ክልሎች ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ዜጎች ሥርዓታዊ በሆነ መልኩ በተመራጭነት እንዳይሳተፉ መደረጉ ነው” ይላል፡፡ 

ለዚህም ማሳያ አድርጎ ያስቀመጠው ከአማራ ክልል ውጭ ባሉ የክልል ምክር ቤቶቹ በክልሉ ተወላጆች ብቻ መያዛቸው እና ብዝኃነትን አለማስተናገዳቸው ነው ብሏል፡፡

የምሁራን መማክርት ጉባዔ በመግለጫው ሀገራዊ ምርጫው ፍትሐዊ፣ አሳታፊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እነዚህ ዜጎች በመራጭነት ብቻ ሳይሆን በተመራጭነትም እንዲሳተፉ የሚያስችል አስቻይ ሁኔታ ሊረጋገጥ ይገባል ነው ያለው፡፡ 

ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ቢሟሉ እንኳን ምርጫው ፍትሐዊ እና ቅቡልነት ያለው ምርጫ ነው ማለት አያስችልም ብሏል፡፡

በተለይም ገዥው ፓርቲ ብልጽግና የክልል ምክር ቤቶች እውነተኛ ሕብረ ብሔራዊ ፌደራሊዝምን የሚያንፀባርቁ እንዲሆኑ በሚወዳደርባቸው ክልሎች ከክልላቸው ውጭ የሚኖሩ ሕዝቦች በተመራጭነት እንዲወዳደሩ የማድረግ ኀላፊነት እንዳለበት አሳስቧል፡፡(አብመድ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top