Connect with us

እሳት የአራት የቤተሰብ አባላትን ሕይወት በላ

እሳት የአራት የቤተሰብ አባላትን ሕይወት በላ
Photo: Facebook

ማህበራዊ

እሳት የአራት የቤተሰብ አባላትን ሕይወት በላ

በኢሉአባቦር ዞን ዳሪሙ ወረዳ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ አራት የቤተሰብ አባላት ህይወት ማለፉን የወረዳው መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት አስታወቀ

የእሳት ቃጠሎው ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አምስት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተገልጿል፡፡

የፅህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ተመስገን ቀልቤሳ ለኢዜአ እንደገለፁት አደጋው የደረሰው ትናንት ሌሊት 9 ሰዓት አካባቢ ያልታወቁ ሰዎች የአንድን ግለሰብ መኖርያ ቤት ከውጭ በመቆለፍ በእሳት በማያያዛቸው ነው፡፡

በአደጋው በመኖርያ ቤቱ ውስጥ የነበሩ እናትና አባት ከሁለት የ3 እና የ10 ዓመት ልጆቻቸው ጋር በእሳት ተቃጥለው ህይወታቸው አልፏል፡፡

ከድርጊቱ ጋር ተያይዞ የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች እስካሁን በቁጥጥር ስር መዋላቸውም ገልፀዋል፡፡

ፖሊስ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን የጉዳዩን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡(ኢዜአ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top