Connect with us

ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቀረቡ

ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቀረቡ

ማህበራዊ

ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ለኢትዮጵያ አቀረቡ

ኢትዮጵያ የሳተላይት ምስል ሽያጩን በራሷ መመሪያ መሠረት ከገዢ ሀገራት ጋር ውል በመፈፀም መሸጥ እንደምትጀምር የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲቲዩት ይፋ አድርጓል።

የህዝብ እንደራሴዎች ምክርቤት የሰው ሃብትና ቴክሎጂ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት የሳተላይቷን ቁጥጥርና መረጃ አሰባሰብ ተመልክተዋል።

የቋሚ ኮሚቴው አባላት ለትውልድ የሚተላለፍ አሻራቸውን በማኖራቸው የኢንስቲትዩቱን ሰራተኞች አመስግነዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ.) ኢትዮጵያን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ባለብዙ ተልዕኮ የሳተላይት መረጃ መቀበያ ተከላ በቅርቡ እንደሚጠናቀቅ ተናግረዋል።

የመቀበያ አንቴናው ሀምሳ ሴንቲ ሜትር የምስል ጥራት እና እስከ አምስት የሚደርሱ የሳተላይቶችን መረጃ በአንድ ጊዜ መቀበል የሚያስችል ነው።

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ዳይሬክተር ጀነራል ሰለሞን በላይ(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ሳተላይት ባመጠቀች በአራት ቀናት ውስጥ ብቻ ስምንት የአፍሪካ ሀገራት የሳተላይት ምስል ግዢ ጥያቄ ማቅረባቸውን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ታህሳስ 10 ያመጠቀቻት ሳተላይት የታሰበላትን ቦታ ይዛ ስራዋን በአግባቡ እየሰራች መሆኑ ተገልጿል።

ሳተላይቷ በቀን አስራ አራት ጊዜ በተዘጋጀላት ምህዋር እየዞረች መረጃ የምትሰበስብ ሲሆን በቀን አራት ጊዜ ደግሞ የሰበሰበችውን መረጃ የመቀበል ስራ ይሰራል፡፡

ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እንዳገኘነው መረጃ በቀጣይ የኮሙኒኬሽን ሳተላይት ግንባታ እንደሚጀመር ተገልጿል።

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top