Connect with us

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንና ለአማኞቹ ምሥጋና አቀረበ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንና ለአማኞቹ ምሥጋና አቀረበ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያንና ለአማኞቹ ምሥጋና አቀረበ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በሞጣ ከተማ በመስጊጅዶች ላይ በደረሰው ጥቃት ላይ በሰጠው መግለጫ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ድርጊቱን በማውገዝ መግለጫ በማውጣት፣ በቦታው በመገኘት የደረሰውን ጉዳት በመመልከትና ማሕበረሰቡን በማፅናናት ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል።

በተመሳሳይ ችግሩ በተከሰተበት ወቅት ችግሩ እንዳይባባስ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ የተወጡ፣ ችግሩ የደረሰባቸውን ግለሰቦች በመንከባከብና በመደገፍ ከጎናቸው የቆሙትን የክርስትና እምነት ተከታዮችን አመስግኗል። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን እና አማኞች በቀጣይም የጋራ ኃላፊነትን እንዲወጡ አሳስቧል።

በሞጣ የተከሰተው ተግባር ከዓለማዊም ሆነ ከኃይማኖታዊ ሕግ የሚፃረርና በሀገርና በክልሉ የነበረውን አብሮነትና የመተሳሰብ ባሕል የሚንድ በመሆኑ በፅኑ እንደሚያወግዘው የገለፀው ምክር ቤቱ፣ የችግሩን ምክንያትና መጠን የሚያጣራ ኮሚቴ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሞጣ የሚጓዝ መሆኑን በመግለጫው አትቷል።

የክልሉ መንግስት ለኮሚቴው ድጋፍ እንዲያደርግ፣ ወንጀለኞችን ለፍርድ እንዲያቀርብ፣ ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች ካሳ እንዲከፍል፣ መስጂዶቹ በአስቸኳይ እንዲገነቡ እንዲሁም በሙስሊሙ ማሕበረሰብ ዘንድ አሉ የሚባሉ ችግሮች እንዲፈቱ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ጠይቋል።

(አሥራት ሚድያ)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top