Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥታ በረራ መጀመሩ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ተባለ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሂዩስተን ከተማ ቀጥታ በረራ መጀመሩ የአሜሪካን ኢኮኖሚ በ100 ሚሊየን ዶላር ያሳድጋል ተባለ
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀጥታ በረራ መጀመሩ የአሜሪካን ኢኮኖሚ ያሳድጋል ተባለ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሜሪካ ውስጥ በሚገኙ ታላላቅ ከተማዎች አገልግሎቱን ለማስፋት በያዘው ዕቅድ መሠረት ባለፈው ሰኞ ዕለት ከሎሜ፣ ቶጎ ወደ ሂዩስተን፣ አሜሪካ ቀጥታ በረራ ጀምሯል።

ይህ ቀጥታ በረራ የአሜሪካ ኢኮኖሚ በየዓመቱ በ100 ሚሊየን ዶላር ገደማ እንዲያድግ ያደርጋል ሲሉ የሂዩስተን አውሮፕላን ማረፊያ ዋና ዳይሬክተር ማሪዮ ዲያዝ ተናግረዋል።

ሄውስተን ውስጥ በሚገኘው ጆርጅ ቡሽ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በተካሔደው የበረራ ማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማርያም በበኩላቸው፣ አየር መንገዱ በቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን በሳምንት ሦስት ቀናት ከቶጎ ወደ ሂዩስተን በረራ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቶጎ 127ኛ መዳረሻው ወደ ሆነችው ሂዩስተን የጀመረው በረራ ከተማዋን ከመላው አፍሪካ፣ መካከለኛው ምሥራቅ እና እስያ ጋር የሚያስተሳስር ነው ብለዋል።

አየር መንገዱ ወደ ሰሜን አሜሪካ የሚያደርገውን በረራ ወደ አምስት እንዲሁም ወደ አሜሪካ ከተማዎች የሚያደርገውን በረራ ደግሞ ወደ አራት አሳድጎታል ሲሉ አክለዋል።

የጋና ኢሚግሬሽን ቢሮ ባልደረባ የሆኑት ቬራ ኦቤንግ ኮናዱ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከምዕራብ አፍሪካ ወደ ሂዩስተን የጀመረው ቀጥታ በረራ ተጓዦች የሚገጥማቸውን የረጅም ሰዓት አሰልቺ ጉዞ ያስቀራል በማለት ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ዘ ሰን

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top