Connect with us

ጠ/ሚ ዐቢይ በኖርዌይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች

ጠ/ሚ ዐቢይ በኖርዌይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች
Photo: Facebook

አለም አቀፍ

ጠ/ሚ ዐቢይ በኖርዌይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በኖርዌይ የሰላም የኖቤል ሽልማትን ከተቀበሉ በኋላ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች

• የኖርዌይ የኖቤል ኮሚቴ ለሰጠኝ እውቅና አመሰግናለሁ፡፡

• ለኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ስምምነት የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የሰላም ቁርጠኝነት ወሳኝ ነበር፡፡

• ይህንን ሽልማት የአፍሪካ ህዝቦችና የዓለም ህዝቦችን ወክዬ ነው የሚቀበለው፡፡

• ከ20 ዓመታት በፊት በኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሬድዮ ኦፕሬተር ነበርኩ፡፡

• ጦርነቱ በርካታ ቀውሶችን አስከትሎ ነበር፡፡

• በኢትዮጵያና በኤርትራ መካከል ለሁለት አስርት ዓመታት ሰላም አልነበረም፣ ሰዎች ተለያይተዋል፣ በርካታ ሰራዊት በሁለቱ አገራት ድንበር ላይ መሽጎ ነበር፡፡

• ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆንኩ በኋላ የሁለቱ አገራት ህዝቦች ልዩነት መቆም እንዳለበት ወሰንኩ፡፡

• ሁለቱ አገራት ጠላቶች እንዳልሆኑ ይልቁንስ ድህነት የጋራ ጣላት እንደሆነ አውቀን ለአገራቱና ለቀጠናው ብልጽግና መስራት ጀመርን፡፡

• መደመር አገር በቀል ሀሳብና የጋራ ብልጽግና ላይ ያተኮረ ሀሳብ ነው፡፡

• የመደመር ጽንሰ ሀሳብ እንደ ዘር ውስጤ የበቀለው በትውልድ መንደሬ በኦሮሚያ ክልል የሚትገኝ በሻሻ ውስጥ ነው፡፡

• በመደመር ጽንሰ ሀሳብ ውስጥ እኛና እነሱ የሚል ነገር የለም፡፡

• ኢትዮጵያኖች በጋራ በመሆናችን ለዓመታት ነፃ አገር ሆነን ቆይተናል፡፡

• የአፍሪካ ቀንድ የአሸባሪዎች ቀጠና እንዲሆን አንፈልግም፣ የሰላም ቀጠና እንጂ፡፡

• የዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በሰላም ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

• ለዴሞክራሲ ግንባታ መንገድ ዘርግተናል፤ በቅርቡ ነፃና ፍትሓዊ ምርጫ እናካሄደለን፡፡

• ለሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች እኩልነት መረጋገጥ አብረውኝ እንዲሰሩ ለኢትዮጵያውያን ጥሪ አቀርባለሁ፡፡ #ebc

Click to comment

More in አለም አቀፍ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top