Connect with us

የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት ለማቋረጥ ማመልከት ተከለከሉ

የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት ለማቋረጥ ማመልከት ተከለከሉ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

የዪኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትምህርት ለማቋረጥ ማመልከት ተከለከሉ

በዩኒቨርስቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች በጊዜያዊት የትምህርት ማቋረጥ (ዊዝድረዋል) ማድረግ እንደማይችሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለዩኒቨርስቲዎች በላከው ደብዳቤ እንዳመለከተው በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር ተማሪዎች የሚያቀርቡትን በጊዜያዊነት ትምህርት ማቋረጥ (ዊዝድረዋል) ጥያቄ ዩኒቨርስቲዎች እንዳያስተናግዱ አሳስቧል፡፡

በተወሰኑ ዩኒቨርስቲዎች በተፈጠሩ ክስተቶች መነሻ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ባሉበት ውይይት ተደርጎ አቅጣጫ ተቆምጧል የሚለው ሚኒስቴሩ ለሁሉም ዩኒቨርስቲዎች በላከው ደብዳቤ ችግሮቹን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑን አስታውሷል፡፡

በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች በተፈጠሩ ችግሮች ውስጥ እጃቸው አለበት ተብሎ የተጠረጠሩ ከ100 በላይ ተማሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው ነው መባሉ ይታወሳል፡፡

ከዛሬ በኋላ ወደ መማር ማስተማር በማይመለሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አሳስቧል፡፡

(ምንጭ :-ሸገር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top