Connect with us

የምግብ ዘይት ምርት አቅርቦትንና ስርጭትን የሚያሻሽል ማስፈጸሚያ መመሪያ ተዘጋጀ

የምግብ ዘይት ምርት አቅርቦትንና ስርጭትን የሚያሻሽል ማስፈጸሚያ መመሪያ ተዘጋጀ
Photo: Facebook

ኢኮኖሚ

የምግብ ዘይት ምርት አቅርቦትንና ስርጭትን የሚያሻሽል ማስፈጸሚያ መመሪያ ተዘጋጀ

የህብረተሰቡን የመሠረታዊ ሸቀጥ ፍላጎት ለማሟላት በመንግስት በኩል የተለያዩ የአሰራር አማራጮች መተግበሩን ተከትሎ በተለይም በ2012 በጀት አመት የመሰረታዊ ሸቀጦችን አቅርቦትና ስርጭት ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡

በዚህም መሠረት የኢፌደሪ ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የህረተሰቡን የመሠራታዊ ፍጆታ እቃ የሆነውን የዘይት ምርት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማሟላት አዲስ መመሪያ አውጥቶ ወደ ክልልና ከተማ አስተዳደር በማውረድ እንዲሁም ክልሎችም መመሪያውን ተከትለው አዲስ አስመጪዎችን በመመልመል ለፌደራል መንግስት እጩዎቻቸውን እንዲያቀርቡ በማድረግ ስራውን ጀምሯል፡፡

ዓላማውም የመሰረታዊ ሸቀጥ የሆነውን የምግብ ዘይት ከህብረተሰቡ የመግዛት አቅም ጋር ተገናዝቦ የአቅርቦት፣ ስርጭት እና የዋጋ ቁጥጥር እየተደረገበት ለህብረተሰቡ ጥቅም ላይ እንዲውሉ አስመጪዎችን መምረጥ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣በመንግስት ድጎማ የሚመጣው የምግብ ዘይት በአገር ውስጥ አምራቾች በሂደት ለመተካት እና ከአቅርቦት እስከ ስርጭት ባለው የንግድ ሰንሰለት ላይ ቁጥጥርና ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ እና በዘርፉ የሚሳተፉ ተዋናዮችን በመምረጥ ሂደት ላይ ግልጽነት ለመፍጠር ክልሎች ከተማ አስተዳደሮችና በተዋረድ የሚገኙ የአስተዳደር አካላት ተሳትፎ አስፈላጊነት የታመነበት በመሆኑ መመሪያው ተዘጋጅቷል፡፡

ነባሮቹ አስመጪዎች ስራቸውን ከመስከረም 30/2012 ዓ.ም ጀምሮ ያቆሙ ሲሆን የህብረተሰቡን የዘይት ፍላጎት አቅርቦት ለማሟላት ሲባል በስራው የረጅም ጊዜ ልምዱ ባላቸው የኢትዮጵያ ኢንድስትሪ ግብአቶች አቅራቢ ድርጅት እና አለ በጅምላ ድርጅት አማካኝት ጊዜያዊ ፈቃድ ተሰጥቷቸው እያስገቡ እንደሚቆዩና በቀጣይም የምልመላ ሂደት ከተጠናቀቀ ወደ ስራ በሚገቡት አስመጪዎች አማካኝነት ምርቱ ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እንደሚሆን ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ የኢንስፔክሽንና ሬጉላቶሪ ዳይሬክቶሬት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ነሐሴ 2011 ዓ.ም የወጣው የምግብ ዘይት አቅርቦትና ስርጭት ማስፈጸሚያ መመሪያ ካሻሻላቸው ጉዳዮች ውስጥ የአስመጪዎችን ቁጥር ከ 10 ወደ 20 የሚያሳድግ እና ቁጥራቸውም ለክልሉ በተመደበው ኮታ መሠረት የሚወሰን መሆኑን ያሳያል፡፡(ንግድና ኢንደስትሪ ሚ/ር)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top