Connect with us

ጠ/ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎችን እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ

ጠ/ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎችን እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ
Photo: Facebook

ህግና ስርዓት

ጠ/ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎችን እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ ሊወስዱ እንደሚችሉ አስጠነቀቁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የክልል፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር አመራሮች እና ህብረተሰቡ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ወደ መረጋጋት የማይመልሱ ከሆነ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠነቀቁ።

በሳይንስና ከፍተኛ የትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት የዩኒቨርሲቲ የቦርድ አመራሮች፣ ፕሬዚዳንቶች እና ሚኒስትሮች በተገኙበት በወቅታዊ የዩኒቨርሲቲዎች ሁኔታ ላይ በትላንትናው ዕለት ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱ ላይ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ምንጭ በማጥናት ዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተደርጓል።

በዚህ ወቅትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መረጋጋት የማይገቡ ከሆነ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዩኒቨርሲቲዎችን ሰላምና ፀጥታ ለመጠበቅና ለማረጋጋት የጥበቃ አቅምን ማዘመን እና በቁጥር ማሳደግ እንደሚገባም አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም በቀላል ወጪ ሊተገበሩ የሚችሉና እንደ አሻራ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን መግቢያ በር ላይ በመትከል የቁጥጥር ስርዓቱን ማዘመን ይገባልም ብለዋል።

ከቁጥጥር ስርዓቱ ባሻገርም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱን እና በአካባቢው የሚገኘውን ህብረተሰብ ማስተሳሰር እንደሚገባም ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዩኒቨርሲቲዎች ችግር በመፍጠር ጉዳት እንዲደርስ በሚያደርጉ ተማሪዎች ላይ መንግሥት ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም ነው የተናገሩት።

ተማሪዎችም ወደ ሞት የሚጋብዟቸውን አካላት ለምን ወደ ሞት እንደሚመሯቸው ቆም ብለው ማስተዋል እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በሚገኙባቸው አካባቢዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከአካባቢው አስተዳደርና ከፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሮችን ቀድመው መከላከል እንደሚገባቸው በዚህ ወቅት ተነስቷል።(ምንጭ :- ፋና)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top