Connect with us

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተነጋገሩ

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተነጋገሩ
Photo: Facebook

ዜና

ጠ/ሚ ዐቢይ ከተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች ጋር ተነጋገሩ

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ በአማራ እና በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልሎች ላይ ከሚንቀሳቀሱ የተፎካካሪ ፖለቲካ ድርጅት አመራር ጋር ዛሬ ከሰዓት ውይይት አካሄዱ።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ውይይቱ ያስፈለገበትን ምክንያት ሲገልጡ «የሁለቱ ሕዝቦች ሠላም ታክቲካል» ሣይኾን «ዛሬም ነገም ከነገ ወዲያም አስፈላጊ በመኾኑ እና የጋራ አጀንዳ ስለኾነ» ነው ማለታቸው ተገልጿል።

አያይዘውም በሁለቱ ክልሎች ኅልፈተ-ሕይወት መከሰቱ እና የንብረት መውደም የሚያስከትሉ ኹኔታዎች መባባሳቸው ውይይቱን አስፈላጊ እንዳደረገው ጠቅላይ ሚንሥትሩ ገልጠዋል። «በዚህ መልክ ከቀጠለ፤ በየቀኑ ሰዎች እየሞቱ ፤ አዛውንቶች እየሞቱ፤ ተማሪዎች እየሞቱ ፤ አብሮ መኖር በየጊዜው በአዳዲስ ቁርሾ ይበልጥ እየተካረረ ከሄደ አደጋ ውስጥ እንዳይገባ እና አብሮነትን ጥያቄ ውስጥ እንዳያስገባ ተመካክረን፤ የጋራ አቅጣጫ ይዘን በጋር እንድንሠራ እና ለሀገር ሠላም፤ ለሀገር ኅልውና፤ ለሕዝቦች አብሮነት በጋራ ብንቆም ስለሚበጅ ነው መድረኩ የተጠራው።»

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ በዜጎች ላይ አንዳችም ዓይነት ጉዳት ሳያስከትሉ ፖለቲካዊ ተሳትፎን የማካሄድን አስፈላጊነት አንስተው፣ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ መሪዎች ሥራቸውን በሚከውኑበት ክልል ሰላምን እና መረጋጋትን ለማስፈን የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል። DW

በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች በዩኒቨርሲቲዎች አካባቢ የሚስተዋለው ግጭት በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ አሳሰቡ፡፡

በአማራ እና በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሱ ሰባት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዩኒቨርሲቲዎችና አንዳንድ የሀገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተዉ የፀጥታ ችግር በሠላማዊ መንገድ እንዲፈታ እና ግጭቱ እንዲቆም በጋራ እንደሚሠሩ አስታወቁ፡፡ ፓርቲዎቹም የአማራ ዴሞክረታሲያዊ ፖርቲ (አዴፓ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ)፤ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ፓርቲ (አብፓ)፣ የአማራ ማኅበራዊ ራዕይ ግንባር (አማራ) ናቸው፡፡

የሁለቱ ክልል ሕዝቦች ለውጥ ለማምጣት በአንድነት የታገሉ እና ሊነጣጠል የማይችል ውሕደት ያላቸዉ ቢሆንም ምንም ዓይነት የጥቅም ግጭት በሌለበት እና በአንዳንድ አካላት በሚነዙ ጉዳዮች ግጭት ውስጥ መግባት እንደሌለባቸው ፓርቲዎቹ አሳስዋል፡፡
ለሠላም መስፈንም የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርዎቹ የበኩላቸውን ለመወጣት እንደተስማሙ አስታዉቀዋል፡፡ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተከሰቱ ግጭቶች አዝማሚያ ወደ ከፋ ነገር ሳይገባ መገታት እንዳለበትም ፓርቲዎቹ በአቋም መግለጫቸው አስታውቀዋል፡፡ የሰባቱን ፓርቲዎች የአቋም መግለጫ የአብን ሊቀ መንበር ደሳላኝ ጫኔ (ዶክተር) አቅርበዋል፡፡

በማንነት ላይ ያተኮሩ ጥቃቶች መፈጸም ጉዳቱ የጋራ በመሆኑ መንግሥትና ሁሉም ኅብረተሰብ ለማስቆም እንዲረባረብም ተጠይቋል፡፡

ከኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዳሉትም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያለዉን አስተሳሰብ ለማቀራረብና ሕዝብ በእኩል ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ለማመቻቸት ሁሉም ኃላፊነት እንዳለበት አስታዉሰዋል፡፡
ከዐማራ ማኅበራዊ ራዕይ ግንባር (ዐማራ) አቶ ስዮም መንገሻ ሕግን ማስከበር የመንግሥት ኃላፊነት ብቻ ባለመሆኑ ብዙኃን መገናኛዎችና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ተሰሚነታቸውን ለበጎ ዓላማ ሊያውሉት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

ከኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) አቶ ዳዉድ ኢብሳ ደግሞ ‹‹ማንኛውም ጥያቄ ሕግን ተከትሎ መከወን አለበት›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡

የሕዝብንና የፖለቲካ ፓርቲዎችን መሠረታዊ ጥያቄ ለመለዬት የሐሳብ ልዩነትን ማቀራረብ ተገቢ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ደሳለኝ ጫኔ (ናቸው)፡፡

የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕረስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ንጉሡ ጥላሁን በበኩላቸዉ በከፍተኛ የትምህርት ተቀዋማት የተፈጠረዉ ግጭት አንዳንዱ ከተማሪው ዓለማና ዕውቅና ውጭ የሆነ በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ሕጋዊ እርምጃ ይወስዳል›› ብለዋል፡፡

የኦሮሞና የአማራ እንዲሁም የመላዉ ኢትዮጵያውያን እሴት ያልሆነ ሁከትና ብጥብጥን በመፍጠር የሚገኝ የፖለቲካ ትርፍ ባለመኖሩ የሀገሪቱን ኅልውና ለማስቀጠል በሠለማዊ መንገድና በውይይት ችግሮችን መፍታት ተገቢ እንደሆነ በፓርቲዎቹ አጽንኦት ተሰጥቶበታል፡፡

ምንጭ:- አብመድ

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top