Connect with us

የፋይናንስ ተቋማትን በመዝረፍ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

የፋይናንስ ተቋማትን በመዝረፍ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

ህግና ስርዓት

የፋይናንስ ተቋማትን በመዝረፍ የተጠረጠሩ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

አሁን አሁን በግለሰቦች እና በመንግስት ተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች እየረቀቁ መምጣታቸዉን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ሰሞኑን ከፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ የተገኘዉም ይህንኑ ያሳየናል፡፡ ከሐምሌ 1/ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሀገረቱ በሚገኙት በተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ላይ የዘረፋ ወንጀል ፈፅመዋል የተባሉ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዉለዋል፡፡

የአንዱን የፋይናንስ ተቋም ካዝና በፌሮ ብረት በመገንጠል ከ1ሚሊየን 5 መቶ 23 ሺህ ብር በላይ የዘረፉትን ጨምሮ በሌሎች ሶስት የፋይናንስ ተቋማት ላይ ሙከራ ያደረጉትን የፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ባደረገዉ ብርቱ ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋሉን በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ምርመራ ዲቪዥን ሃላፊ ኢንስፐክተር ሳሙኤል ሰለሞን ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ማህበራዊ ሚዲያን ተጠቅመዉ የማጭበርበር ተግባራት የፈፀሙ ግለሰቦች እንዳሉም ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ ግለሰቦቹ አሳሳች ቃላቶችን በመጠቀም እና ከኢትዮጵያ ዉጭ እንደሚኖሩ በማስመሰል የወንጀሉ ተጎጂ ከሆኑት ሰዎች ጋር ትዉዉቅ ማድረጋቸዉ ተገልጿል፡፡ የተለያዩ አጓጊ ዕቃዎች ከዉጭ ሀገራት እንደተላከላቸዉ በማስመሰል በማህበራዊ ሚዲያ አሳይተዋቸዋልም ተብሏል፡፡

ግለሰቦቹ ከኢትዮጽያ አየር መንገድ ስልክ እንደተደወለላቸዉ በማስመሰል “የተላከላችሁን ዕቃ ከአየር መንገድ ወደ ገቢዎች እና ጉሙሩክ የሚተላለፍበት ገንዘብ ያስፈልጋቸዋል” በማለት አስቀድሞ ባዘጋጁት ሐሰተኛ መታወቂያዎች እና የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ሂሳብ ደብተሮች( Account numbers) በርካታ ገንዘብ እንዲገባላቸዉ አድርገዋል ተብለዋል፡፡

ፖሊስ በግለሰቦቹ ላይ ባደረገዉ ብርበራ 30 የሚደርሱ የ13 የፋይናንስ ተቋማት የሂሳብ ደብተሮች፣ ሐሰተኛ መታወቅያዎች፣ 5 መቶ 40 ዶላር እና ከ162 ሺህ ብር በላይ እንዲሁም መጠኑ ያልታወቀ የናይጀሪያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬት ገንዘብ ልይዝ ችሏል፡፡ የማጭበርበር ተግባሩን ፈፅመዋል የተባሉት ሁለት ኢትዮጵያዊ እና አምስት በስደተኞች ካምፕ የሚኖሩ የዉጭ ሀገር ዜግነት ያላቸዉ ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዉሎአቸዋል፡፡ የሰዉ እና የሰነድ ማስረጃዎችን በማደራጀትም በዓቃቤ ህግ በኩል ክስ እንዲመሰረትባቸዉ አድርጓል፡፡

በመጨረሻም ማንኛዉም ሰዉ ማህበራዊ ሚዲያን በጥንቃቄ እና በሃላፊነት ስሜት መጠቀም እንዳለበት ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡ ከተለያ ተቋማት የሚሰጡ ሰነዶችም በህጋዊ መንገድ ታይተዉ መሰጠት እንዳለባቸዉ ፖሊስ አሳስቧል፡፡

(ምንጭ፡-የፌደራል ፖሊስ)

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top