Connect with us

በቤንሻንጉል ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት አንድ የፖሊስ አመራር አባል ተገደለ

በቤንሻንጉል ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት አንድ የፖሊስ አመራር አባል ተገደለ

ህግና ስርዓት

በቤንሻንጉል ያልታወቁ ታጣቂዎች በከፈቱት ጥቃት አንድ የፖሊስ አመራር አባል ተገደለ

ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ፀረ ሰላም ሀይሎች ባደረጉት ተኩስ አንድ የፖሊስ አመራር ህይወት ማለፉን ፓሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መሀመድ ሀምደኒል ግድያዉን በማስመልከት ለጋዜጠኖች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በቀን 05/2012 ዓ/ም ከቀኑ 5፡00 አካባቢ ከአሶሳ ወደ ካማሺ በመሄድ ላያ ያለ የግል መኪና ማንነታቸዉ ያልታወቁ የታጠቁ ሀይሎች ከካማሺ መገንጠያ ማቃ ቢላ ተብለዉ በሚጠራዉ አካባቢ መኪናዉን በማስቆም ተኩስ የከፈቱ ሲሆን 1 የካማሽ አመራር ፖሊስ ምክትል ኢንስፔክተር ታደሰ ጀዋኔ የተባለዉ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል ብሏል፡፡

በአካባቢዉ የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ሀይሎች ህዝቡ በአሁኑ ሰዓት ተረጋግቶ ያለዉን ሁኔታ በማየትና ሰላሙን ለማደፍረስ ታስቦና ሆን ተብሎ የተደረገ እንጂ ከካማሺ ህዝብ ጋር ህዝቡ ምንም አይነት ችግር እደሌለበትም አነስቷል፡፡

በመሆኑም የተጠረጠሩ ሀይሎች በኦሮሚያ የፀጥታ አካላት የተያዙ ሲሆን ከዚህ ከፀረ ሰላም ሀይል ጋር የራሳቸዉን ተልዕኮ የሚያራምዱ ሀይሎች እንዳሉ መረጃ የሰጡት ኮሚሽነር መሀመድ ከአጎራባች ክልሎች በተለይ ከአማራና ኦርሚያ ጋር በጋራ በመሆን የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመቅረፍ እየሰሩ እንደሆነ አነስቷል፡፡

በተመሳሳይም በቀን 03/2012 ዓ/ም በመተከል ዞን በዳንጉር ወረዳ አጋርቲ ክትሊ በሚባል ቀበሌ 1 ሰዉየ ገንዘብ የያዘ መሆኑን ሌቦች በማየት እንደተመታና ተጠርጣሪዎችም በቁጥጥር ስር መዋላቸዉን ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም በዚህ ወቅት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያና የገንዘብ ዝዉዉር በከፍተኛ ሁኔታ እንዳለ በማንሳት በአሁኑ ሰዓት ያለዉን ተስፋ ሰጪ አንፃራዊ ሰላም ለማስጠበቅ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚናፈሱ ወሬዎችን ወደ ጎን በመተዉ ህዝቡ ከመንግሰት ጎን መቆም አለበት የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

(ምንጭ የቤንሻንጉል መንግስት ኮምኒኬሽን)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top