Connect with us

በታክስ ስወራና ህገ-ወጥ ደረሰኞችን የሚጠቀሙና የሚያትሙ 166 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ

በታክስ ስወራና ህገ-ወጥ ደረሰኞችን የሚጠቀሙና የሚያትሙ 166 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ
Frontera.net

ህግና ስርዓት

በታክስ ስወራና ህገ-ወጥ ደረሰኞችን የሚጠቀሙና የሚያትሙ 166 ድርጅቶች ይፋ ተደረጉ

በገቢዎች ሚኒስቴር ክትትል ስደረግባቸው የቆዩ ታክስን ለመሰወርና ህገ-ወጥ ተመላሽ ለመጠየቅ ህገ ወጥ ደረሰኞችን የሚጠቀሙ ሀሰተኛ ማንነት ያላቸው 166 ድርጅቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡

በዛሬው እለት በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና በህግ ተገዢነት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ በተሰጠው መግለጫ በነፍስ ወከፍ ከ51 ሚሊየን ብር በላይ ግብይት የነበራቸው ነገር ግን ባዶ፣ ኪሳራና ተመላሽ ከሚጠይቁ ደርጅቶች መካከል 16 ድርጅቶች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገ ነው፡፡

ከ166 ድርጅቶች መካከል 136 ያህሉ ከ 6ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ማድርጋቸውን በመረጃ ቋት ውስጥ መገኘቱን ነው የተናገሩት፡፡

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጉዳዩን አስመልክተዉ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የንቅናቄና አጠቃላይ የለዉጥ እንቅስቃሴ የመጣዉን አዎንታዊ ዉጤት አጠናክረን በማስቀጠል በህገ ወጥ ድርጊት ላይ ተሳትፈዉ እየተንቀሳቀሱ ያሉ አካት ላይ የሚወሰደዉ የህግ ማስከበር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ሚኒስትሯ አክለዉም እነዚህ ህገወጥ ድርጅቶች በዋናነት ሃሰተኛ ደረሰኝን የሚያቀርቡ በመሆኑ ግብር ከፋዩ ማንነታቸዉን አዉቆ ምንም አይነት ደረሰኝ ከነሱ እንዳይቀበልና ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱም እንዳያቀርብ አሳስበዋል፡፡

ድርጅቶቹ ያለደረሰኝ ግብይት ማከናወን፣ ከተጠቃሚ የሚሰበሰበውን ታክስ ለራስ ጥቅም ማዋልና ግብይትን በመደበቅ መንግስት ሊያገኝ የሚገባውን ታክስ አሳጥተዋል፡፡

በመግለጫው የውድድር ሜዳውን ለማስተካከል የህግ ተገዢነት ስትራቴጂን አጠናክሮ በመፈጸምና ህጋዊ እውቅና ለታማኝ ግብር ከፋዮች እውቅና ለታማኝ ግብር ከፋዮች በመስጠት ከማስተማር ህጋዊ እርምጃ እስከ መውሰድ የሚችልበት አቋም ላይ ይገኛል፡፡

(ምንጭ ገቢዎች ሚኒስቴር)

Click to comment

More in ህግና ስርዓት

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top