Connect with us

ታላቋ አሜሪካ ምን ፈልጋ ነው?….

መላኩ ብርሃኑ

ነፃ ሃሳብ

ታላቋ አሜሪካ ምን ፈልጋ ነው?….

ታላቋ አሜሪካ ምን ፈልጋ ነው?….
(መላኩ ብርሃኑ)

በኢህአዴግ ጊዜ “አሸባሪው ኦነግ ከተማዋን ሊያሸብር እየተዘጋጀ መሆኑ በብሄራዊ መረጃና ደህንነት ተደርሶበታል። ዕቅዱ ከሽፏል ።ህዝቡ ግን ጥንቃቄ እንዲያደርግ” የሚሉ መግለጫዎች ይወጣሉ።

በማግስቱ የሆነ አውቶቡስ ውስጥ ወይም ታክሲ ላይ ወይም መንገድ ዳር ወይም መስሪያ ቤት አካባቢ ቦምብ አስቀምጠው “ለሽብር የተዘጋጀ ቦምብ ሳይፈነዳ ተደርሶበት በባለሙያዎች ከሸፈ” የሚል ዜና እንዲሰራ ያደርጋሉ ።አንዳንዴም በዚህ አይነት”ስቴጅድ ክራይም” ለፕሮፓጋንዳ ብቻ ተብሎ አንድ ያልታደለ ንጹህ ህይወት ይገበራል።

ይህ ቴክኒክ ህዝቡን በአንድ አካል ላይ ለሚወሰድ እርምጃ አስቀድሞ በስነልቡና ማመቻቸት ነው። አንዳንዴ ‘ስቴጅድ ክራይም’ ይባላል ተግባሩ።

አሜሪካ “በኢትዮጵያ ላይ ሰማይ እየወደቀ ነው” እያለች ነው….እንደኢህአዴግ ያለ ‘ለእርምጃ አስቀድሞ የማመቻቸት’ ቴክኒክ እየተጠቀመች እንደሆነ ይሰማኛል። እየወደቀ ነው ያለችውን ሰማይ ራሷ ጦር አስገብታ ልትጥለው ፈልጋለች። ይህንን በሌሎችም ሃገራት ላይ አድርጋው አሳይታናለች። ለሃገሪቱም ለህዝቦቿም ጠላት ማብዛት ብቻ ካልሆነ በቀር ትርፉ አልታየኝም።

መቼም ከዚህ ውጪ ኢትዮጵያ ውስጥ ሰማይ ሲወድቅ አሜሪካ ብቻዋን ያየችው ህልም ካለም ትንገረንና እኛም እንጠንቀቅ።

‘ታላቋ አሜሪካ’ በርግጥስ ምን ፈልጋ ነው?….በርግጥ ምክንያት ያደረገችው ሁሉ ቢፈታና ህወሃትና መንግስት ቢደራደሩ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያዞረችውን ፊት ትመልሰዋለች የሚል የዋህ ይኖር ይሆን?

የአሜሪካ ፖለቲካ ለራስ ጥቅም ማስፈጸሚያ ብቻ የሚውል መሳሪያ እንጂ ለሌሎች ሰላም የቆመ ዘብ አይደለም ።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top