Connect with us

የአሜሪካና ሸሪኮቿ ሩጫ

ወገን እንቁረጥ?!
Photo: Social media

ማህበራዊ

የአሜሪካና ሸሪኮቿ ሩጫ

የአሜሪካና ሸሪኮቿ ሩጫ

(ፋሲል የኔዓለም )

አሜሪካና ሸሪኮቿ ህወሃትን ለማዳን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አንቶኒ ብሊንከን፣ አሜሪካ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ከመጣል ጀምሮ፣ በእጇ ላይ ያሉ ማስገደጃዎችን ሁሉ ትጠቀማለች ብለዋል። የአፍሪካ ህብረትን፣ የአውሮፓ ህብረትን፣ የጀርመንና ፈረንሳይን ባለስልጣናት አነጋግረዋል። የአማራና የአፋር አካባቢዎች ሲወረሩ ዝም ያሉት ምዕራባውያን፣ አሁን ጥርሳቸውን አግጥጠው መነሳታቸው፣ ትክክለኛ ፍላጎታቸውን ያሳያል።

ኒውዮርክ ታይምስ እንደተለመደው የአብይን አስተዳደር የሚያወግዝ ዘገባ ይዞ ወጥቷል። ጻድቃን ገ/ትንሳይ ” ይህ ጦርነት የተራዘመ አይሆንም ብሏል።  “እስካሁን ያለውን የፖለቲካ፣ የወታደራዊና የዲፕሎማሲ ሁኔታ የሚቀይር ነው” ሲልም  ተናግሯል።  የኢሳያስ ጦር እስካሁን ጣልቃ ባይገባም፣ የጨዋታውን ሁኔታ የሚቀይረው እሱ በመሆኑ፣ አለም የኢሳያስን ሁኔታ አንድ ይበልልን ሲል ጻድቃን ተማጽኗል።

የኢትዮጵያ ጦር ከቻይና፣ ኢራንና የናይትድ አረብ ኢሜሬትስ ድሮን እንዳገኘ ዘኒዮርክ ታይምስ  ዘግቧል። መረጃውን ከየት እንዳገኘው ግን አልገለጸም። በእኔ እይታ ዘገባው በአሉባልታ፣ ስድብና ጨጫታ የተሞላ ነው።

ቢቢሲም የህወሃትን የውጭ ጉዳይ ቃለ አቀባይ የሆነውን ፍሰሃ አስገዶምን አነጋግሮ ዘገባ ሰርቷል። ፍሰሃ “በጦር ጄት፣ በድሮን፣ በታንክና በሌሎችም ከባድ መሳሪያዎች ጥቃት እየተፈጸመብን ነው” ሲል እየተጎላደፈ ተናግሯል። ይህ ሰው በተመድ የኢትዮጵያ ተጠሪ ነበር። እንዴት አድርጎ በውጭ ቋንቋ ሃሳቡን ሲገልጽ እንደነበር እግዜር ይወቅ። ህወሃት በመሆኑ ብቻ ያለቦታው የተሸሞ ሰው እንደነበር፣ ከንግግሩ መረዳት ይቻላል። ለማንኛውም ሰውየው፣ ዛሬውኑ ድርድር ለማድረግ ዝግጁ ነን ብሏል። ጦርነቱ እንዲቆምም ለምኗል። ” ማን ያደራድረን የሚለው በሁለተኛ ደረጃ የሚታይ ነው፣ አሁን ጦርነቱ ይቁም” ሲል ጠይቋል።

በዚህ ሁሉ መሃል የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ዝምታን መርጧል። አለም ግን እየተንጫጫና እየነደደ ነው። ይህ መሬት ላይ ስላለው ነገር ብዙ ነገሮችን ይነግረናል።

 

Click to comment

More in ማህበራዊ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top