Connect with us

“ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው!!”

እስክንድር ነጋ

ነፃ ሃሳብ

“ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው!!”

“ፍትህን ማዘግየት ፍትህን መንፈግ ነው!!”
(ፋሲል የኔዓለም)

በባልደራሱ መሪ እስክንድር ነጋ ላይ የሚታየው የፍርድ ሂደት መጓተት በምንም መልኩ ተቀባይነት የለውም። አቃቢ ህግ የእስክንድርን ጥፋት የሚያሳይ ተጨባጭ ማስረጃ ማቅረብ ካልቻለ፣ በፍጥነት ሊለቀው ይገባል።

ፍርድ ቤትም የዜጎችን መብት የማስከበር ግዴታውን መወጣት አለበት። ይህን የምለው ባለጉዳዩ እስክንድር ስለሆነ አይደለም። ማንም ይሁን ማን፣ አንድ ተከሳሽ ግልጽ በሆነና በሚያምንበት የዳኝነት ስርዓት ሊስተናገድ ይገባል።

የእስክንድርን የፖለቲካ አቋምና አካሄድ እንደማልደግፍ ይታወቃል። ይህ ደግሞ መብቴ ነው። እስክንድርም የእኔን አካሄድ አለመደገፉ መብቱ ነው። እሱን ስላልደገፍኩ ልወገዝ ወይም ስለደግፍኩት ደግሞ ልመሰገን አይገባም።

የእስክንድርን የፖለቲካ አቋም ስላልደገፍኩ፣ በፍርድ ሄደት መጓተት ሲቸገር ሳይ ዝም እላለሁ ማለት አይደለም። በእኔ እምነት አሁን ላይ አቃቢ ህግ የፍርድ ሂደቱን የሚያጓትትበት መንገድ፣ እንጸየፈው የነበረውን የወያኔ ዘመን የፍርድ ሂደት የሚያስታውሰን ነው። ወደዛ አስከፊ ስርዓት በፍጹም አንመለስም!

ዜጎች በወንጀል ተጠጥረው ከተያዙ በኋላ ጉዳያቸው በፍጥነት ተጣርቶ ውሳኔ የሚያገኙበት መንገድ ካልተመቻቸ፣ የምንመኘውን ስርዓት በፍጥነት መገንባት አንችልም። የፖለቲካ አስተሳሰባቸው ምንም ይሁን ምን፣ በእስር ላይ ያሉ ዜጎች ለአንድ ቀንም ቢሆን በፍርድ ሄደት መጓተት ሊንገላቱ አይገባም። ፍትህን ማዘግየት፣ ፍትህን መንፈግ ነው።

ፎቶ:- እስክንድር ነጋ

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top