Connect with us

 የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ማሳሰቢያ

በትግራይ ክልል የሲቪል ሰዎችን ሁኔታ ለማሻሻል አፋጣኝ እርምጃዎች ሊወሰዱ ይገባል

ዜና

 የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ማሳሰቢያ

 የሰብዓዊ መብት ኮምሽን ማሳሰቢያ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከየካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘውን የወጣት ሙሃመድ ዴክሲሶንና በሱ መዝገብ የተከሰሱትን ሁለት ሰዎችን የፍርድ ቤት ሂደት በቅርበት በመከታተል ላይ ይገኛል። የጅማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ተከሳሾቹን በነጻ አሰናብቶ ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም አሁንም በእስር ላይ መሆሆቸውን ማረጋገጡን ጠቅሷል፡፡

ስለሆነም ኮሚሽኑ እስረኞቹ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአስቸኳይ ከእሰር እንዲለቀቁ እየጠየቀ የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ እንዲከበር በድጋሜ አሳስቧል፡፡

መሀመድ ዴክሲሶ የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ባስመረቀበት መድረክ  እነ ጃዋር መሐመድ ከእስር እንዲፈቱ ከመጠየቁ ጋር በተያያዘ ታስሮ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡ ፍርድ ቤት ወጣቱን  ቢያሰናብተውም አስፈጻሚው አካል ሊያስፈጽም አልቻለም፡፡  

የመሐመድ ዴክሲሶ ጠበቃ በአንድ ወቅት ለዶይቼ ቬለ እንዳሉት ደንበኛቸው በመድረኩ የተናገረው የመናገር ነጻነት አንዱ ማሳያ ቢሆንም ሁከት በማነሳሳት እና ከታጣቂ ኃይሎች ጋር ግንኙነት አለው በሚል ወንጀል ተጠርጥሮ በፖሊስ መታሰሩን አረጋግጠው ነበር፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ አለመከበሩ እንዳሳሰበው ባመለከተበት መግለጫው ፍርድ ቤት ተመራቂው የጅማ ዩኒቨርሲቲ እንዲለቀቅ የሰጠው ውሳኔ እንዲከበር በድጋሚ ጠይቋል።

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top