Connect with us

 የምዕራባዊያን ውትወታ፤ ከህውሓት ጋር ተደራደሩ – የሞኝ ፈሊጥ

የምዕራባዊያን ውትወታ፤ ከህውሓት ጋር ተደራደሩ - የሞኝ ፈሊጥ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

 የምዕራባዊያን ውትወታ፤ ከህውሓት ጋር ተደራደሩ – የሞኝ ፈሊጥ

 የምዕራባዊያን ውትወታ፤ ከህወሓት ጋር ተደራደሩ – የሞኝ ፈሊጥ

(ያሬድ ኃ/ማርያም ~ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች)

ህወሓት በከፍተኛ እና በአለም አቀፍ የሰቆቃ (atrocity) ወንጀሎች መጠየቅ ካለባቸው እኩይ ቡድኖች አንዱ ነው። ለረዥም ዓመታት ህወሓት ከነተባባሪዎቹ የፈጸማቸው የመብት ጥሰቶች በአግባቡ ተሰንደዋል። የተጠያቂነት ባህል በአገር ደረጃ ማስፈን ባለመቻሉ ነው እንጂ ህወሓት ድሮ ነበር እንደ ድርጅትም፤ አመራሮቹም እንደ ግለሰብ ለፍርድ መቅረብ የነበረባቸው። 

ይህን ክፍተት በመጠቀምም ህውሓት ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥም እጅግ ዘግናኝ የሆኑ የመብት ጥሰቶች ሲፈጽም እና የሚፈጽሙ አካላትንም በይፋ ሲደግፍ ቆይቷል። በተለይም የትግራይን ሕዝብ አሁን ላለበት አስከፊ ስቃይ መዳረጉ ህውሃትን በሕግ እንዲፈርስ እና በሕይወት የተረፉትንም አመራሮቹ ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያስደርግ ሁኔታ ከበቂ በላይ ተሟልቷል።

ምዕራባዊያን በጦርነቱ ሳቢያ በትግራይ ሕዝብ ላይ ለደረሰው ከፍተኛ ጉዳት እና ሰቆቃ የሚያሳዩት ተቆርቋሪነት ከመስመር አልፎ ህወሓትን ለድርድር እንዲመጣ የመጣር አዝማሚያ ማሳየታቸው በምንም መስፈርት ቢሆን አግባብነት ያለው አይደለም። የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መዳፈሩ ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ደረጃም ወንጀልን እና ህወሓት መሰል ወንጀለኛ ድርጅቶችንም የሚያበረታታ አጉል አድራጎት ነው። 

እንደ ህወሓት ያሉ በንጹሐን ደም የጨቀዩ ድርጅቶችንም ከተጠያቂነት እንዲያመልጡ በር ይከፍታል። ህወሓትን የኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ሳይሆን የአለም አቀፍ ማህበረሰቡም ጭምር ተጠያቂ ሊያደርገው የሚገባ ቡድን ነው። ለበርካታ ዓመታትም የታገልነው ይህ ቡድን ከነአባሪዎቹ በሕግ ፊት ተጠያቂ እንዲሆን ነበር። 

የአለም አቀፍ ማህበረሰቡ በትግራይ ክልል ውስጥ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ ለማስተካከል፣ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚፈጸሙ አስከፊ የመብት ጥሰቶችን ለማስቆም እና በመብት ጥሰት የተሳተፉ አካላትን በሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት፣ ግፊት እና ውትወታ አግባብነት ያለው ነው። 

ከዛ ባለፈ ህወሓት ነፍስ እንዲዘራ የሚደረገው ጥረት ግን በህወሓት የወንጀል አድራጎት ባለቁ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎች ህይወት መቀለድ ነው። ህወሓት እንደ ድርጅት መፍረስ፤ አመራሮቹ ደግሞ እንደ የኃላፊነት ደረጃቸው ለፍርድ መቅረብ ነው ያለባቸው።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top